ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን…

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን…

  • Post comments:0 Comments

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት በመተካት የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በትኩረት እንሰራለን፤ከለውጡ ወዲህ በኢኮኖሚ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ትልቅ እምርታ አሳይተዋል። ባለፉት በርካታ ዓመታት ስንዴ ማምረት እየቻልን ባለማምረታችን በውጭ ምንዛሪና በልመና ከውጭ ስናስገባ ነበር። በተደረገው ማሻሻያ ስንዴን በአገር ውስጥ ለመተካት የተሰራው ሥራ ውጤት እያስገኘ ነው።

ስንዴ የምትለምን አገር ስንዴን ወደ ውጭ እልካለው የምትልበት ደረጃ ደርሳለች። በሚቀጥለው ዓመት ስንዴን ወደ ውጭ ገበያ እንልካለን። ይህም በግብርናው መስክ ሰፊ የለውጥ ሥራ በመሰራቱ የመጣ ውጤት ነው። የጓሮ እርሻ ከቤተ መንግሥት ጀምሮ በአዲስ አበባ በስፋት እየተሰራበት ነው። አትክልትና ፍራፍሬ ከአረንጓዴ አሻራ ጋር ተያይዞ ሰፊ ሥራ ተሰርቶበታል።

በዘንድሮው ዓመት ብቻ አትክልትና ፍራፍሬን ወደ ውጭ በመላክ 82 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ይህም ትልቅ እምርታ ነው። በጓሮ አትክልት በፍራፍሬ፣ በስንዴ ትልቅ ለውጥ መጥቷል።

Leave a Reply