ለውጡ በተለያዩ ፈተናዎች…

ለውጡ በተለያዩ ፈተናዎች…

  • Post comments:0 Comments
ለውጡ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖም የተሻለ ነገር አሳይቷል፤ ከሪፎርሙ በኋላ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል።ለውጡ የተመዘገበው ግን ከኮቪድ ወረርሽኝ ባለፈ ሰው ሰራሽ ችግሮች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ሁነን ነው።ብዙ ፈተናዎችን ብናልፍም ካጋጠሙን ችግሮች አንጻር የሰራነው የተሻለ ነው።
በተለይ ባጋጠመን አገር የማፍረስ ውጊያ ብዙ ችግር ተፈጥሯል፤ ውጊያው እንዲሁ በቀላል የሚታይ ሳይሆን አገርን ከመፍረስ የታደገና፤ ኢትዮጵያ አበቃላት ያሉትን ሃሳባቸውን የቀለበሰ ነው።የአገር ውስጡን ችግር ጨርሰን እፎይ ሳንል የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ኢኮኖሚው ላይ ጫና አሳድሯል። ከዚህ ባለፈ የውጭ ጫናም እንደነበረ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል።
ያለፍናቸው ብዙ ችግሮች የተጋረጡብን በወጉ ሳንደራጅና ተቋማት ሳንፈጥር ነው። ተመሳሳይ ችግሮች ወደፊት ቢቀድሙን ግን ከትላንቱ በበለጠ የምንፈታበት አቅም አሁን ላይ አለን።እያንዳንዱ መከራ ግን የእራሱ የሆነ ዕድል ይዞ መጥቷል። ኮሮና ስለመጣ መሬት ጦም አይደር ብለን እንድንነሳ አድርጓል።

Leave a Reply