ስንደማመጥ ከባዱ ነገር ቀላል ይሆናል፤

ስንደማመጥ ከባዱ ነገር ቀላል ይሆናል፤

  • Post comments:0 Comments

አገራችን የገጠማችን ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ብርቱ ትግል ላይ መሆኑን ሁላችንም የምናስተውለው እውነታ ነው፡፡ እነዚህ የተደቀኑ ችግሮች መፍቻው በሕዝቦች ላይ አንድነትና መተባበር እንዲሁም ምክንያታዊነት መግባባት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህንን የሁለንተናዊ ችግራችን መፍትሄ የሆነን ቁልፍ በትክክል መጠቀም ደግሞ የእኛው ፋንታ ነው። ለችግራችን መፍትሄ የሚሆኑ ጉዳዮችን በስክነት መለየት ብሎም መተግበር ይገባናል።

መግባባት እንኳን በአገር ደረጃ በግለሰብ ደረጃ በሰከነ መንገድ ካልተመራ አደጋው የከፋ ይሆናል፡፡  እያንዳንዳችን አገራችን በብልጽግና ማማ ከፍ እንድትል እና ለሁላችንም የሚትመችና አገር እንድትሆን እንመኛለን፡፡ ያለችንን አንድ አገር ሕልውናውንና አንድነቷን ማስጠበቅና የተከበረችና የተፈራች እንድትሆን ማድረግ ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ ነው፡ ኢትዮጵያውያን ያልገዛ ባይነታቸውና ነጻነታቸው መነሻ አንድነትና ትብብር ነው፡፡

ለዓመታት በከንቱ የፈሰሰ የአባይ ወንዝን ወደ አገሩ ዕደገትና ልማት እንዲውል ያደረገው የትብብራችንና የአንድነታችን ውጤት ነው፡፡ ዛሬም በድጋፍ በድህነት እንድንማቅቅ የሚፈልጉ ሃይሎች እንዳሉ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ በ “NO MORE” ዘመቻ ያስመዘገብነው ድል የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡ ስንደማመጥ ከባኩ ቀላል ይሆናል፡፡

ከሰሞኑ የአፍሪካ ልማት ፕሬዘዳንት አኪውሚ አዴሲፕ ኢትዮጵያ የማምረት አቅም 650 ሺህ ሄክታር ደርሷል ፤በቀጣይ ዓመት ከ2ሚሊየን ሄክታር በላይ በማልማት ቢያንስ ከ1.5 እስከ 2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ወደ ጎረቤት አገራት ለመላክ ታቅዷል፤ የሚገርም ነው፤ ሲሉ የሙገሳ ንግግር በማቅረባቸው ታዳሚን በጭብጨባ አዳራሽን አናውጦታል፡፡

ይህም በስንዴ ምርት ኢትዮጵያ አፍሪካን ጭምር መመገብ የሚያስችል አቅም እየፈጠረች መሆኑ በቡድን ሰባት የልማት ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተሰጠው ምስክርነት ነው። ይህም በተባበርና በመደማመጥ የአገራችንን አንደነት ከማስጠበቅ አልፎ ውስጣችንን በደንብ እንድናይ እና ያለን እምቅ ሃብቶች በመጠቀም በወንድማማችነትና በአብሮነት በመጓዝ የአገራችንን ብልጽግና እውን ልናደርግ ይገባል፡፡

Leave a Reply