በመደመር ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ፤  /በሚራክል እውነቱ/

በመደመር ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ፤ /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments

ሀገር ሀገር ሆና ልታድግ የምትችለው የእያንዳንዳችን ዕውቀት፣ጉልበትና ገንዘብ ተደምሮ በምናበረክተው አስተዋፆኦ ልክ ነው ቢባል መሳሳት አይሆንም፡፡ እያንዳንዳችን በቅንጅት የምንሰራቸው በርካታ የቤት ስራዎች አሉብን፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ሀሳብ ምክንያታዊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ሊከበር ይገባዋል ፡፡ይህ ማለት ለህዝብና ለሀገር የሚያመጣው መሰረታዊ ለውጥ አሳማኝ መሆኑ ተረጋግጦ ማለት ነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ለሁላችንም የምትበቃ መሆኗን ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊረዳው የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ማለት በአንድነትና በመተሳሰብ ወገባችን እስኪጎብጥ እጃችን እስኪሻክር ድረስ መስራት የምንችል ከሆነ ከድካማችን የምናገኘው ፍሬ የሁላችንም ይሆናል ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በጋራ ተደምረን ሀገርንና ህዝብን ማሳደግን እንደምንችል ሁሉ አንድ ከሚያደርጉን ይልቅ በትንንሽ ጉዳዮች ስራ ፈተን በልዩነቶቻችን ላይ ጊዜ የምናባክን ከሆነ ውድቀታችንም የጋራ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡

ለውጡ ፍሬ ማፍራት ከጀመረና ህዝቡም ፍሬውን ማጣጣም ከጀመረበት ካላፉት አራት አንስቶ የማይታመን ግን ደግሞ መሰረታዊና ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ወጣቱ፣ጎልማሳው፣አዛውንቱ፣ተማሪው ፣መምህሩ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንግዲህ ወዲህ የሚፈልገውና የሚመኘው ሰላምንና ፍቅርን፣ አንድነትን ፣መተሳሰብንና መከባበርን እንዲሁም በጋራ ተነስቶ አገርን መገንባት ብቻ እንደሆነ ነው።

ከዚህ አኳያ ይህ በገሀድ የታየው ለውጥ እንዳይቀለበስና ተጠናክሮ እንዲቀጥል የእያንዳንዳችን ሚና ምን መሆን አለበት  ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል፡፡ የዚህ ሁሉ ጥያቄ መልሱ ወይም ቁልፉ መደመርና መደመር ብቻ ነው። ያለን ብቸኛው አማራጭ አንድ ብቻ ነው። እሱም በጋራ ተነስተንና እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንወዳት ኢትዮጵያችንን በሁላችን አሻራ መገንባትና በኢትዮጵያ ምድር ዘለዓለማዊ አንድነትና ሰላምን ማስፈን ነው።

ሁላችንም እንደምንረዳው  ዛሬ ላይ በብልጽግና ማማ ላይ ከፍ ብለው አንቱታን ያተረፉ ሀገራት እዚህ ደረጃ ላያ መድረስ የቻሉት ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው ህዝብን አክብረው ሀገርን አስቀድመው  ሌት ተቀን መስራት በመቻላቸው መሆኑ መቼም ለማንም ይጠፋዋል ማለት አይቻልም፡፡ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአስቸጋሪ በርሃማነት ወደ ምዳራዊ ገነትነት የተለወጠችውን ዱባይን ማንሳት ህዝብ በአንድነት ሲደመር ተዓምር መስራት እንደሚችል ማሳያ ይሆናል፡፡

የሁላችንም ምኞትና ዓላማ ሊሆን የሚችለው በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ በመፍጠር የህዝባችንን ህይወት መቀየር ነውና ህዝብንና ሀገርን ሊጠቅሙ ለሚችሉ ለመልካም ነገሮች ሁሉ መደመር መቻላችን ለነገ የማይባል የዛሬ የቤት ስራ ሊሆን ይገባል መልዕክታችን ነው፡፡

 
@Prosperity

Leave a Reply