አቋሙ በምንም ሁኔታ…

አቋሙ በምንም ሁኔታ…

  • Post comments:0 Comments

አቋሙ በምንም ሁኔታ የማይለዋወጥ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሌት ተቀን የሚጥረው ብልፅግና ትክክለኛና እውነተኛ ፌደራሊዝም እንዲተገበር አበክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡እጅግ ተለዋዋጭና ፈታኝ ችግሮች ቢደራረቡም፣ህዝቡ ብልፅግና ፓርቲ ከሚመራው መንግስት ጎን በመሆን የሕግ የበላይነት እንዲከበርና ሕገ ወጦች አደብ እንዲገዙ፣ የውስጥ ተላላኪዎች ከውጭ ሃይሎች ጋር ተዳምረው የሚፈጥሩትን ጫና ለመቀነስ ከምንጊዜውም በላይ አንድነታችንን ልናጠነክር ይገባል፡፡

ዘመን ተሻጋሪ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ውጤት ለማምጣት ርብርብ እያደረገ የሚገኘውና የህዝብ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ እጅግ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እያለ እንኳ መሰረታዊና ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገቡን ቀጥሎበታል፤ ዳሩ ከሰራቸው ስራዎችና ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ገና ወገብ የሚያጎብጡ አያሌ የቤት ስራዎች ቢኖሩበትም፡፡

ኢትዮጵያዊያን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ለህግ የበላይነት በሁሉም ቦታ መከበር፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ፈተና የማያላላው አንድነታቸውን ይበልጥ እንዲያጠነክሩ፣እንደ አገር ለሚገጥሙን  ፈተናዎች በጋራ መመከት እንድንችል በተደራጀና ለውጭ ሃይሎች ክፍተት በማይፈጥር መልኩ መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

ሀገራዊ ጉዳዮች ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳ መሆኑን በአግባቡ ተረድተን ትኩረት መስጠት ከቻልን እና ለጋራ ብልፅግና በጋራ መነሳት ከቻልን በሩቅ ያየነውን ብልጽግና እዚሁ በኢትዮጵያችን ላይ ዕውን ሆኖ እናየዋለን፡፡

Leave a Reply