ወጣትነት የአይበገሬነትና የአልሸነፍባይነት ምልክት ነው፤  /በሚራክል እውነቱ/

ወጣትነት የአይበገሬነትና የአልሸነፍባይነት ምልክት ነው፤ /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments

ሰው በህይዎት ዘመኑ በርካታ ነገሮችን ሰርቶ ያልፋል፡፡ ሀገርን ከማፈራረስ ጀምሮ እስከ ሀገርን በከፍታ ማማ ላይ እስከማስቀመጥ ድረስ ማለት ነው፡፡በአስተውሎ የተሞላና ምክንያታዊ የሆነ አዕምሮ ዜጎችንና ሀገርን ሲያለማ በክፋትና በተንኮል የታወረ ጭንቅላት ደግሞ ሀገርን በማተራመስና ገፅታዋን በማጥፋት ዜጎችን የሰቀቀን  ህይዎት እንዲያሳልፉ ምክንያት ይሆናል፡፡

ለመለወጥም ሆነ ላለመለወጥ፣ ለመገንባትም ሆነ ለማፍረስ፣ ለጥሩውም ሆነ ለመጥፎው፣ ለደግነትም ሆነ ለክፋት አዕምሯችን ክፍት ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገሩ ይህን ያህል ዓለምን በቴክኖሎጂና በጥበብ ማነፅ የቻለ አዕምሮ የምንጠቀምበት መንገድ ነው፡፡

ለመልካም ነገር ስንጠቀምበት ለሰው ልጆች ግርምት ሊፈጥሩ የሚችሉ በርካታ ደጋግ ሀሳቦችን አመንጭቶ ወደ ተግባር በመቀየር ዓለምን በእጁ መዳፍ ያስገባል፡፡ ያላደለው አዕምሮ ደግሞ ከመልካምና ትልልቅ ጉዳዮች ይልቅ በትንንሽ ነገሮች ተጠምዶ ሀገርንና ህዝብን ሲያተራምስ ይውላል፡፡

ሰው የውሳኔ ውጤት እንደመሆኑ መጠን የምንፈፅማቸው ድርጊቶችም የአዕምሯችን ውጤቶች ናቸው፤ምን ያህሎቻችን ይህንን ተረድተን ይሆን? አዕምሯችንን ለብሩህ ነገር በመጠቀም ለወገናችንና ለሀገራችንን ተስፋ መሆናችንን ልናሳይ ይገባል፡፡ ታዲያ ከፍጡራን ሁሉ ተለይተን ሰው የመሆናችን ምክንያት ምንድን ነው? በአስታዋይነትና መራመድ ካልቻልን፡፡

የሰው ማንነት ከማግኘትም ከማጣትም በላይ ነው፡፡ ሰው ስላገኘ ሀገሩንና ህዝቡን የሚወድ ስላጣ ደግሞ በወንድሙና በሀገሩ ላይ ጦር የሚያዘምት ከሆነ እንዴት “ሰው” የሚለውን ማንነት ልንሸከም እንችላለን? እኛ ወጣቶች በሚመጥነን ቦታ ልንቆም ይገባል፡፡ ምክንያቱም ወጣትነት የአይባገሬነትና የአልሸነፍባይነትና  ምልክት ነውና፡፡

ወጣትነት መልካምነት ሊሆን የሚችለው በአስታዋይነትና በምክንያታዊነት ዘውድ መድፋት ሲችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ አዕምሯችንን ደግ ደጉን በመመገብ በጊዜ ሂደት አብሮን የሚመጣ እንጂ ስንፈልግ የምናገኘው ቁስ አይደለም፡፡

የሀገሬ ሰው “በቆሎ ሳይሆን ቡናን ሁነህ ለመፈጠር ሞክር” ይላል፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በቆሎ እዛው ተዘርቶ ለምርት ሲደርስ አካባቢው ያለ ሰው ብቻ ነው ሊጠቀምበት የሚችለው ፡፡ከእዛ ባለፈ ሀገርን በማስተዋወቅ ብሎም የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ ቅንጣት ያህል አስተዋፆኦ ሊኖረው አይችልም፡፡ ከዚህ አንፃር  ቡና ለሀገራችን የሚያበረክተውን አስተዋፆኦ ሀገሪቱን በበጎ ጎኑ ከማስተዋወቅ ጀምሮ ለሀገሬ እስትንፋስ እስከሆነው የውጭ ምንዛሬ ድረስ ማበርከት የሚያበርክተውን አዎንታዊ ሚና መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናልና ብተዎው ይሻላል፡፡ለዚህ ነው ከበቆሎ ይልቅ ቡናን ሁነህ ተፈጠር የሚባለው፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ወጣቶች በዕድሜ ዘመናችን ስንኖር በተሰጠን አዕምሯዊ ፀጋ መልካም መልካሙን በማሰብ ወንድማማችነት በማጎልበት አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር ለላቀ ሀገራዊ ዕድገት ሚናችንን ልንወጣ ይገባል፤ምክንያቱም ሀገር ከሙዚቃ፣ ከስነ-ግጥም፣ከፊልም፣ከፉከራና ከቀረርቶ የዘለለ ሀያል ትርጉም ስላለው ማለት ነው፡፡

በመግባባት ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት በመገንባት እንደ ሀገር እየገጠመን ያለውን የፅንፈኝነት አስማሚያ በጋራ ልንመክት ይገባል ፡፡ሀገራችን ሰላሟ የተረጋገጠ ፣የበለፀገች፣ ወጣቶቿ በመግባባት መንፈስ አብሮነታቸውን በተግባር በማሳየት ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡

የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ መስራት ከእኛ ከወጣቶች በተግባር የሚጠበቅ እውነታ ነው፡፡በፖለቲካና በኢኮኖሚ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ፣ለራስ ጥቅምና ክብር የማይጓጉ፣ሀገር የማገልገል ፍላጎት ያላቸው፣በፖለቲካና በጠቅላላ ዕውቀታቸው የተመሰገኑ ወጣቶችን ማፍራት ጊዜው የሚጠይቀን ግዴታችን ነው፡፡

በአጠቃላይ ከክፋትና ከአሉታዊ አስተሳሰቦች የሚገኝ ትርፍ የለምና ወጣቶች በወጣትነት ዘመናችሁ መልካም ነገሮችን በመስራት የሀገር ባለአደራ መሆናችሁን የምታሳዩበት ጊዚያችሁ አሁን ነው፡፡

Leave a Reply