You are currently viewing ፊትን ወደ ትናንት አዙሮ…

ፊትን ወደ ትናንት አዙሮ…

  • Post comments:0 Comments

ፊትን ወደ ትናንት አዙሮ እንዴት ነው ወደ ነገ መጓዝ የሚቻለው? በእርግጥም ለጥያቄው መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡በዚህ በሰለጠነ ዘመን አብሮነታችንን ማጎልበት ሲገባን የኋላውን እያነሳን ለፀብ ከተጋበዝን መደማመጥ አቅቶን አንዳችን በሌላችን ላይ ጣታችንን የምንቀስር ከሆነ በእርግጥስ የወደፊቱ እኛነታችን ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል፡፡በአንድ ጉዳይ ላይ ተቸንክረን መቆም ለውጥ አያመጣም፡፡ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በዛሬው ልፋታችንና ድካማችን ነገን አስበን ስንሰራ መሆኑን ማሰብ ተገቢ ነው፡፡

 

አቅጣጫችን ወደፊት ብቻ ነው፡፡ወደ ኋላ እየተመለከቱ እርስ በእርስ መነታረክ ዛሬያችንን ያባክንብናል፡፡የህዝብ ሰላምና የሀገር መረጋጋት ግድ የማይሰጣቸው አንዳንድ ጽንፍ የረገጡ ሀይሎች ወደፊት አስቦ ሀገርን ወደ ተሻለ ከፍታ ከማሻገር ይልቅ በትናንቱ አስተሳሰባቸው ተቸንክረው ይሄው ዛሬ ድረስ በዜጎች መካከል መቃቃርን በመፍጠር ላላስፈላጊ ግጭት፣ግድያና ሞት ምክንያቶች ሆነዋል፡፡

 

ሕዝባችን ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሀገር ሰላም፣ ለልማት በጥቅሉ ለሁለንተናዊ ብልጽግና እያሳዬ ያለው ፍላጎት ከጊዚያዊ ግጭቶች ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አንሶ አያውቅም፡፡ የኢትዮጵያዊያን የመልማት ፍላጎት ከማንኛውም ከፋፋይ አጀንዳ ይበልጣል፤ይሄ ሐቅ ነው፡፡ ይሄንን ለሺህ ዓመታት ተከባብሮና ተዋዶ የኖረን ጽኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮችን እንዳይደገሙ አድርገን እንደምንፈታቸው ብልጽግና እምነቱ ከፍ ያለ ነው።

ምላሽ ይስጡ