አቅጣጫችን ወደፊት…

አቅጣጫችን ወደፊት…

  • Post comments:0 Comments

አቅጣጫችን ወደፊት ብቻ ነው፡፡ወደ ኋላ እየተመለከቱ እርስ በእርስ መነታረክ ዛሬያችንን ያባክንብናል፡፡የህዝብ ሰላምና የሀገር መረጋጋት ግድ የማይሰጣቸው አንዳንድ ጽንፍ የረገጡ ሀይሎች ወደፊት አስቦ ሀገርን ወደ ተሻለ ከፍታ ከማሻገር ይልቅ በትናንቱ አስተሳሰባቸው ተቸንክረው ይሄው ዛሬ ድረስ በዜጎች መካከል መቃቃርን በመፍጠር ላላስፈላጊ ግጭት፣ግድያና ሞት ምክንያቶች ሆነዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ራሱን በአዳዲስ አስተሳሰቦች እየለወጠ ሀገርን ከፈተና ማቅ አውጥቶ ከድህነት ወደ ብልጽግና ማማ ለማሻገር እየታተረ የሚገኝ ህዝባዊ ፓርቲ ነው፡፡ምንጊዜም የኢትዮጵያን ስኬቷን ሳይሆን ውድቀቷን፣ከፍታዋን ሳይሆን የቁልቁለት ጉዞዋን፣ጥንካሬዋን ሳይሆን ድክመቷን የሚመኙ እንቅልፍ የሌላቸው ጠላቶች ህዝቦቿን ሲሻቸው በብሔር አሊያ በሃይማኖት በመከፋፈል የማያባራ የግጭት ቅርቃር ውስጥ ለማስገባት ሲኳትኑ ዛሬም ድረስ ይስተዋላል፡፡ ዳሩ ከፍላጎት የዘለለ መቼም የማይሳካ ሕልም ብቻ ቢሆንም፡፡ይህ መሆን የሚችለው ግን በጋራ ከእኩይ ድርጊታቸው መመከትና መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡

ሕዝባችን ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሀገር ሰላም፣ ለልማት በጥቅሉ ለሁለንተናዊ ብልጽግና እያሳዬ ያለው ፍላጎት ከጊዚያዊ ግጭቶች ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አንሶ አያውቅም፡፡ የኢትዮጵያዊያን የመልማት ፍላጎት ከማንኛውም ከፋፋይ አጀንዳ ይበልጣል፤ይሄ ሐቅ ነው፡፡ ይሄንን ለሺህ ዓመታት ተከባብሮና ተዋዶ የኖረን ጽኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮችን እንዳይደገሙ አድርገን እንደምንፈታቸው ብልጽግና እምነቱ ከፍ ያለ ነው።

Leave a Reply