You are currently viewing በአንድ አገር ውስጥ አንድ…

በአንድ አገር ውስጥ አንድ…

  • Post comments:0 Comments

በአንድ አገር ውስጥ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ኖሮም አያውቅም፤ሊኖርም አይችልም፡፡ ስለሆነም በሁሉም ነገር መግባባት ከቶም አይቻልም፤ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው የራሱ ምልከታና ግምት አለውና፡፡ ሆኖም ግን ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በማድረግ እንደ አገር ለድርድር በማይቀርቡ ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መክረን ለአገር ቀጣይ ሰላም፣ልማትና ብልጽግና ደጀንነታችንን ልናሳይ ይገባል፡፡

በመስቀል አደባባይ የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት ይካሄዳል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ “የፖለቲካ ሥርዓቱ የአሸናፊ ሳይሆን የመግባባት እንዲሆን አብረን እንሠራለን። በንግግር እና በምክክር ለአንገብጋቢ ችግሮች መፍትሔ እናገኛለን። አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን። ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙርያ የምንፈታበት ይሆናል” ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል። ይኸም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን” ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቃል ገብተዋል፡፡

ይህ አካታች የምክክር ሒደት ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን የሚያካትት፤ በፖለቲካ ልሒቃን መካከል ብቻ የሚደረግ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ያገናዘበ አጠቃላይ ሒደቱ አካታች እና አሳታፊ እንዲሁም በኢትዮጵያውያን እየተመራ ሀገር በቀል መፍትሔዎች ለማፍለቅ ታልሞ የሚከናወን ስለመሆኑ የብልጽግና ፓርቲም ሆነ መንግስት በተደጋጋሚ እየገለጸ ይገኛል፡፡

ስለሆነም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ አካታች ብሔራዊ የምክክር መድረክ ስኬታማነት የየበኩላችንን አስተዋጾኦ በመወጣት የታሪክ ተካፋይ ልንሆን ይገባል፡፡

ምላሽ ይስጡ