የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የጽህፈት ቤት ሃላፊ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የጽህፈት ቤት ሃላፊ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

  • Post comments:0 Comments

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የጽህፈት ቤት ሃላፊ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የጽህፈት ቤት ሃላፊ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ በመካሄዱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህና የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚስተር ፒተር ላም ቦዝ በአዲስ አበባ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሚስተር ፒተር ላም ቦዝ የብልጽግና ፓርቲ የተሳካ ጉባኤ በማካሄዱ እና አዲስ አመራሮችን በመምረጣቸው የእንኳን ደስ አላችሁ ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት እጅግ ጥልቅና መጠነ ሰፊ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን የምንግዜው የኢትዮጵያን ወዳጅና አጋር እንደሆነችና ፓርቲያቸውም ይህን የዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት ሚስተር ፒተር በቀጣይ በሁለቱ ፓርቲዎችና ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚያግዙ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላችው የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ነቅናቄ በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያውና ታሪካዊ ጉባኤ በመገኘት አጋርነታቸውን በመግለጻቸው አመስግነዋል፡፡

አቶ አደም አያይዘውም የኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ግንኙነት ስትራቴጂያዊና በወቅታዊ ጉዳዮችና በስርዓት ለውጥ ጭምር የማይለዋወጥ መሆኑን በተግባር የተፈተነ እንደሆነ አውስተው የብልጽግና ፓርቲም ይህን መጠነ ሰፊ የሆነውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አረጋግጠውላቸዋል፡፡

በመጨረሻም በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦችን በመለዋወጥና በቀጣይ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተደጋግፈው ለመስራትና ልምዶችን ለመለዋወጥ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

Leave a Reply