ብልፅግና ፓርቲ እንደአንድ የፖለቲካ ተቋም መዳረሻ ግቡን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ አድርጎ የተደረጃ ሀገራዊ ፓርቲ ነው፡፡ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵ ብልፅግና ማለት የጥቂቶች ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሆነና መሆንም ይገባዋል ብሎ በሚገባ ያምናል፡፡ በመሆኑም የብልፅና ፓርቲ እሴቶች ከሆኑት መካከል አንዱ “ብልፅግና ለሁሉም፤ ሁሉም ለብልፅግና“ የሚለውን እሴት እናገኛለን፡፡
“ብልፅግና ለሁሉም፤ ሁሉም ለብልፅግና“ የሚለው የፓርቲው እሴት መነሻው ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ከዳር ቆመው የሚመለከቱበትና ጥቂቶች ብቻ የሚጠቀሙበት ሳይሆን መላው ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሁሉም ሀገራዊ ጉዳዮች ያለአንዳች ገደብ በእኩልነት ተሳትፎ በማድረግ በእኩል ተጠቃሚ መሆን ይገባቸዋል ከሚል ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንደሆነ መረዳት ይገባል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ይህንኑ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት3 ከጅምሩ አንስቶ በተግባር እውን ለማድረግ በሀገራችን ሁሉንም ዜጋ ተሳታፊ ማድረግ ያስቻለ የፖለቲካ ምህዳር በመፍጠር አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ከፍቶ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ብልፅግና ማለት ውስን ዜጎች ወይም ጥቂት ቡድኖች ብቻ የሚበለፅጉበት ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙየመላው ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ብልፅግና ማለት መሆኑን በሚገባ መረዳት ይገባል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ሊሆን የሚችለው እንዲሁ የሚገባው በሁሉም አቅጣጫ ከዳር እስከ ዳር የሚገኙ መላው ኢትዮጵያውያን ዜጎች በሚገባ ተሳታፊ በመሆን የበኩላቸውን ድርሻ ሲያበረክቱ እንደሆነ ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ማለት የመላው ኢትዮጵያውያን ማለት በመሆኑና የኢትዮጵያ ብልፅግናም እውን የሚሆነው በመላው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በመሆኑ ምክንያት “ብልፅግና ለሁሉም፤ ሁሉም ለብልፅግና“ የሚለውን የፓርቲውን እሴት ትክክለኛነትና ተገቢነት በሚገባ የሚያሳይ ይሆናል፡፡