የብልጽግና ፓርቲ መለያ እሴቶች
three steps modern business infographic template design

የብልጽግና ፓርቲ መለያ እሴቶች

  • Post comments:0 Comments

የብልጽግና ፓርቲ መለያ እሴቶች

ህብረ ብሔራዊ አንድነት፡-አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ነው፡፡ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣የሐይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማህበረሰብ ማለታችን ነው፡፡

የዜጎች ክብር ፡-ኢትዮጵያዊያንን በእኩል ዓይን የሚያይና የሚዳኝ፣ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ፣የብሔር ብሔረሰቦች መብትና ነጻነት የሚረጋገጥበት፣እውነተኛ ህብረ ብሔራዊነት የሚረጋገጥበት፣በዋና ዋና የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ዜጋ ውሳኔ ላይ ተሳታፊ የሚሆንበት፣የሀብት ስልጣንና የመብት ክፍፍሉ ፍትሃዊ የሚሆንበት የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ስርዓት መፍጠር፣አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት፡፡

ነጻነት፡-ዜጎች የራሳቸውን ህይወት ርዕይ የመምረጥ፣በመረጡት መንገድ የመኖር መብት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡የዜጎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ የአገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍታት፡፡የዜጎችን የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመጻፍና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣የመምረጥና የመመረጥ መብቶችን ማረጋገጥ፡፡

Leave a Reply