You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች የቅድመ ጉባዔ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ

የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች የቅድመ ጉባዔ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ

  • Post comments:0 Comments
የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች የቅድመ ጉባዔ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ
በጉባዔ ዝግጅት ሂደት በተካሄዱ ሀገር አቀፍ የፓርቲ ኮንፈረንሶች መላው የብልፅግና ፓርቲ አባላት በጉባዔው በቀጥታ በመሳተፍ የሚወክሏቸውን መርጠዋል፡፡ እነዚህ የሕዝብ ውክልና የተሰጣቸው የጉባኤ አባላት በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ውይይቱ እስከ መጋቢት 1/2014ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በጉባዔ ሪፖርት እና በቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ሪፖርት እንዲሁም በፓርቲው ህገ ደንብና ፕሮግራም ላይ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ውይይቱን ያስጀመሩት የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ የቅድመ ጉበዔ ውይይቱ በፓርቲያችን አመራር ሀገራችን ስኬቶች ባስመዘገበችበት ወቅት እና በበሳል አመራር ሰጪነት ልንፈታቸው በሚገቡ ሀገራዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነን የምናካሂደው ነው ብለዋል፡፡
በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰጠንን ሃላፊነት እና እምነት ከዳር ለማድረስ በወንድማማችና አብሮነት መንፈስ መስራት ይገባናል ያሉት አቶ አደም በቅድመ ጉባዔው የሚካሄደው ይህ ውይይት ለአንደኛ ጉባዔያችን ስኬታማነት ቁልፍ አስተዋፆ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በውይይቱ 1600 ጉባኤተኞች እየተሳተፉ ናቸው፡፡

ምላሽ ይስጡ