ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ጉልበት  /በሚራክል እውነቱ/

ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ጉልበት /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments
ፓን አፍሪካኒዝም መላውን የዓለም ጥቁር ህዝብ እንደ አንድ አፍሪካዊ ቤተሰብ የሚመለከት አስተሳሰብ ወይም ንቅናቄ ነው።ንቅናቄው በዋነኝነት የቅኝ ግዛት መስፋፋትን (የነጭ የበላይነት) ለመዋጋትና አፍሪካዊ አንድነትን ለማጠናከር የታለመ ነበር።
ፓን አፍሪካኒዝም በፖለቲካ፣በስነ ጽሁፍ፣በሙዚቃ፣በባህልና በመሳሰሉት ዘርፎች የተቃኘ ሰፊ ንቅናቄ ነበር።ይህ ንቅናቄ መሰረቱን በአገረ አሜሪካ ያድረግ እንጂ የንቅናቄው መንፈስና ብርታት ኢትዮጵያ ነች።በዚህም ኢትዮጵያ በፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ውስጥ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ሃይልና ኩራት ተደርጋ ትወሰዳለች።
የፓን አፍሪካኒስት ንቅናቄ ባለበት ወቅት ብዙ ጥቁሮች ከኢትዮጵያ ጎን ቆመዋል።የዚህም ዋነኛው ምክንያት ፓን አፍሪካኒዝምግቡ ላደረገው የአንድ ጠንካራ አፍሪካዊ ማህበረሰብ ግንባታ ኢትዮጵያ እንደ ማዕዘን ድንጋይ መታየቷ ነው።የዚህ አስተሳሰብና እምነት ገፊ ምክንያት ደግሞ ኢትዮጵያ በማንኛውም የቅኝ ገዢ ኃይል ያልተንበረከከች ብቸኛ አገር በመሆኗ ነው።
ኢትዮጵያ በተለያየ መልኩ የተቃጣባትን የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን በሚገባ መመከቷና አይበገሬ ሆና መገኘቷ የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ መልሶ እንዲያንሰራራ አድርጓል።ብሔራዊ ነፃነት፣ ሉዕላዊነትና በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት የማይታለፉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ቀይ መስመሮች ሆነው እንዲቀጥሉ ኢትዮጵያ በጽናት እየታገለች ነው።
ኢትዮጰያውያን ከቀድሞ ጀምሮ ሉዓላዊነቷን የማታስደፍርና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነትም ስትሟገት የቆየች አገር ናት ስትሆን ዘንድሮም በተለያየ መልኩ የገጠሟትን የውጭ ተጽዕኖና የውስጥ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን በጽናት በመታገል ላይ ትገኛለች።
ሁኔታዎችን ለማላሰላስ ብለን አንዷ ላይ እንኳን ሸብረክ ካልን ብዙ መዘዞችን ያስከትላል።
አገሪቱ አሁንም አዲሱን የቄሳራዊ ስርዓት ዝንባሌን በፅናት መታገልና መቋቋም አለባት። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ፀንቶ በመቆም በሌሎች መለስተኛ ጉዳዮች ላይ መመካከር ይቻላል። ነገር ግን ግልጽ የሆነ ቀይ መስመር መቀመጥ አለበት ።እነዚህ ቀይ መስመሮች እንዳይታለፉም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ትግል በማደረግ ላይ ይገኛሉ።
አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን በሚገባ እየመከተች ቢሆንም ወደፊት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል፣ የህብረሰተቡን አንድነት ለመከፋፈል አጀንዳ የሚወረውሩትንና ሽኩቻ የሚፈጥሩትን በማስታገስ የአገሪቱን አንድነት ማስጠበቅ ያስፈልጋል።
ምዕራባዊያን ከጥንት ጀምሮ በአፍሪካ አገራት ላይ ጣልቃ ገብተው የአፍሪካዊያንን ህይወት ቢያመሰቃቅሉም ኢትዮጵያ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍላ ነፃነቷን አስጠብቃለች። ምዕራባዊያኑ በአገራችን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትን የሚቀናቅን አስተዳደር ከተቋቋመ ወዲህ ለእነሱ የእጅ አዙር ብዝበዛ የሚመች ሁኔታ ስላልፈጠረላቸው ጫና ሲፈጥሩ ቆይተዋል።
በተቻለ መጠን የለመዱትን ፈቃድ ፈጻሚ መንግሥት ለማስቀጠል ካልሆነም ደግሞ ያለውን ለዓላማቸው ተገዢና ተላላኪ አስተዳደር ለመፍጠር ጥረዋል። የአሁኑን ጣልቃ ገብነት ልዩ የሚያደርገው የግል ወዳጅነት ላይም ጭምር የተመሰረተ መሆኑን አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በአቋሟ ፀንታ በመቆየቷ እዚህ ደረጃ የደረሰች ሲሆን ጉዳዩ የፓን አፍሪካኒዝም ዝንባሌ እየጫረ ነው። በዓለም አቀፍ ግንኙነት እውነቱን ለዓለም ማሳወቅ፣ መከራከርና መደራደር የወደፊት አቅጣጫ ሆነው መቀጠል አለባቸው።

Leave a Reply