‹‹ኢትዮጵያውያን ለውይይት ዕድል በመስጠት ለጦርነት የሚጋለጡበትን ሁኔታ መቋጫ እንዲያገኝ ማድረግ ይገባቸዋል›› ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ

  • Post comments:0 Comments
‹‹ኢትዮጵያውያን ለውይይት ዕድል በመስጠት ለጦርነት የሚጋለጡበትን ሁኔታ መቋጫ እንዲያገኝ ማድረግ ይገባቸዋል›› ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ
ለውይይት ዕድል በመስጠት ኢትዮጵያውያን ለግጭትና ላለመግባባት ብሎም ለጦርነት የሚጋለጡበትን ሁኔታ መቋጫ እንዲያገኝ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ፡፡
ዶክተር ቢቂላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ለውይይት በቂ ዕድል በመስጠት ኢትዮጵያውያን ለግጭትና ላለመግባባት ብሎም እስከ ጦርነት ለሚደርስ ችግር የሚጋለጡበት ሁኔታ መቋጫ እንዲያገኝ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
ከውጭ ጣልቃ ገብነት በፀዳ መንገድ በውይይት ችግሮቻቸውን መፍታት የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው፡፡ ያለማንም የውጭ ጣልቃ ገብነት ቁጭ ብለው እንዲወያዩ ዕድል መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል ዶክተር ቢቂላ፡፡
እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያውያን ከውጭ ጣልቃ ገብነት በጸዳ መንገድ አጀንዳዎችን እየቀረፁ ቁጭ ብለው እንዲወያዩ ዕድል መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ ሂደቱ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚችሉበት እድል ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ችግራቸውን ለመፍታት የሚያስችል አቅም፣ ብቃት፣ ስነ ልቦና የቆየ ባህል እንዲሁም እሴት በሁሉም ብሔሮች ውስጥ በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ያለ መልካም ሀብት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እስከ አሁን በጣም መሠረታዊ መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው፤ ለግጭት እና ላለመግባባት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ፣ የሀገረ መንግሥቱን ቀጣይነት ፈተና ውስጥ ሊጥሉ የሚችሉ እና በየጊዜው ሰዎች እየተነሱ ለኩርፊያ ለግጭት የሚዳርጉ ነገሮች አሉ ብለዋል፡፡
በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያውያን ሰፊ ጊዜ ወስደው ቢወያዩባቸው መስማማት ላይ የሚደረሱባቸው መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡
እነዚህ ለግጭት መንስኤ የሆኑ ነገሮች ያለምንም ችግር ወደ ፊት መጥተው በጠረጴዛ ዙሪያ አጀንዳ ሆነው ለውይይት ቀርበው ኢትዮጵያውያን ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሰፊ ጊዜ ወስደው የሚወያዩባቸው ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በአገራችን በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ጭምር ተቃርኖ፣ ልዩነት፣ የአረዳድ እና የግንዛቤ እንዲሁም የአስተሳሰብም ጭምር ችግር መኖሩን አስታውሰው፤ ነገር ግን አብዛኞቹ የሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በውይይት መግባባት ላይ ይደረሳል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።አገራዊ አጀንዳዎቹ ምንም ቢከብዱ በውይይት አብዛኛዎቹ ላይ መግባባት ይቻላል የሚል እምነት እንዳላቸውም አመልክተዋል፡፡
ጉዳዩ እከሌ የሚባል ፓርቲ እከሌ ከሚባል ፓርቲ ጋር ስለተጋጨ ወይም የእነእከሌ ብሔር ከእነእከሌ ብሔር ጋር ተቃርኖ ስላለው፤ የእነከሌ ፍላጎት እና የነእከሌ ፍላጎት ስለማይገናኝ የሚል አለመሆኑን እና ምክክሩ ትንሽ ሳይሆን ትልቅ ሃሳብ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህ ኢትዮጵያውያን ቁጭ ብለው እንዲወያዩ የታሰብበት በጣም ሩቅ አሳቢ ፕሮጀክት በስኬት መጠናቀቅ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply