“ኢትዮጵያ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ሰላማዊ ሀገር እንድትሆን መስራት አለብን” አቶ ርስቱ ይርዳ~የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

“ኢትዮጵያ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ሰላማዊ ሀገር እንድትሆን መስራት አለብን” አቶ ርስቱ ይርዳ~የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

  • Post comments:0 Comments
“ኢትዮጵያ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ሰላማዊ ሀገር እንድትሆን መስራት አለብን” አቶ ርስቱ ይርዳ~የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
 
የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠልና የህዝባችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት ሰላማዊ ሀገር እንድትሆን አመራሩ በከፍተኛ ኃላፊነትና ትጋት ሊሠራ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ።
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሐዋሳ ከተማ እየተወያዩ ነው።
ኢትዮጵያውያን በኃይል ለማፈራረስ የተቀናጁ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎችን መላው ኢትዮጵያዊን የመከቱበት የህልውና ጦሪነት ኢትዮጵያን በአገራቸው ጉዳይ የማይደራደሩ አንድ አቋም ያላቸው ህዝቦች መሆናችንን ዛሬም ዓለም እንድመሰክር አድርገናል ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበት ጦሪነቱ ሀገሪቱ በለውጥ ማግስት የሰነቀችውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማደናቀፍ የውጭና የውስጥ ኃይሎች ያጠመዱት ወጥመይድ መሆኑን ገልጸው፣ መላው የሀገራችን ህዝቦች የህልውና ጦሪነቱን የመከትነው ያክል በጠላቶቻችን የታቀደው ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ውጥኖችን ለማሳካት በትጋት መስራት እንዳለብን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
በህልውና ጦሪነቱ ሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የገለጹት አቶ ርስቱ በጦሪነቱ በህልውና ላይ የመጣ በመሆኑ ህልውናችንን ለመመከት የፈጠርነውን አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና አቅም አድርገን መጠቀም አለብን ሲሉም ገልጸዋል።
ዛሬ የተከፈተው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መድረክ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት መወያየት ተጨማሪ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply