You are currently viewing የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀመሩ

የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀመሩ

  • Post comments:0 Comments

የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀመሩ

እንደሚታወቀው ተገደን የገባንበት የህልውና ጦርነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል ተጠናቋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 3 ቀናት የሚቆየው ውይይትም የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡

የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብአዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃት መፍታትና በአግባቡ መምራትም እኩል ትኩረት ያገኛሉ ተብሏል፡፡

በህልውና ጦርነት ሂደት ውስጥ ያገኘናቸው አገራዊ አንድነት ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ልምድ በጋራ ዓላማ ለጋራ የመስራት ልምድ የአመራር ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቁርጠኝነት ለአገራችን ዘላቂ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ የመምራት አስፈላጊነት ላይ ከፍተኛ አመራሩ በጥልቀት ይወያያል፡፡

በውይይቱ የድህረ ጦርነት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ የፀጥታና ሰብአዊ ሁኔታዎች በብቃት በመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምላሽ ይስጡ