ስለ አካታች አገራዊ ምክክር…

ስለ አካታች አገራዊ ምክክር…

  • Post comments:0 Comments
• ስለ አካታች አገራዊ ምክክር እንደ አገር በተለያዩ አካላት ሲቀነቀን የነበረው ከአሸባሪው የህወኃት ቡድን ጋር ወደ ጦርነት ከመግባታችን በፊት ነው፤መነሻውም አካታች አገራዊ ምክክር ለአገራችን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፤በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሊፈቱ የማይችሉ ትላልቅ ጉዳዮች አሉ፤በፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ብቻ የማይፈቱ ሰፋፊ አጀንዳዎች አሉ ከዚህ አኳያ አካታች አገራዊ ምክክር ያስፈልጋል ተብሎ ሲቀነቀን ቆይቷል፡፡
 
• የለውጡ አመራር ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ይህንኑ አጀንዳ ሲያቀነቅን ቆይቷል፤እንደ መሪ ፓርቲም፣በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ደረጃ፣በተለያዩ ሲቪክ ማህበራትም አካታች አገራዊ ምክክር ለአገራችን በጣም አስፈላጊ እንደሆን ሲነሳ ቆይቷል፤ስለዚህ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የተነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ያለውን ጦርነት ለመቋጨትና ችግሩን ለመፍታት ተብሎ የቀረበ ጉዳይ አይደለም፡፡

Leave a Reply