ቤታችንን በራሳችን….በእጃችን!

ቤታችንን በራሳችን….በእጃችን!

  • Post comments:0 Comments
ህወሃት እንደ አበደ ውሻ በየደረሰበት ያገኘውን እየተናከሰ ብዙ ከሰውነት የወረዱ ተግባራትን ፈጽሟል፡፡ ይህ የሽብር ቡድን በደረሰበት ሁሉ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንጹሃን መኖሪያ ቤቶች፣ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን አውደሟል፡፡ ዘርፏል፡፡
ህወሃት በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ የጥፋት በትሩን ያሳረፈባቸው የህዝብ መገልገያ ተቋማት ወደቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ ኢትዮጵያውያን በህብረት እየሰሩ ነው፡፡ በአማራ እና አፋር ክልል የወደሙና የተዘረፉ ጤና ተቋማት ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ በኢትዮጵያውያን እጆች መሟላት የሚገባቸው ግብዓቶች እየተሟሉ እና እየተጠገኑ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ነው፡፡ በቀጣይም ሁሉም የጤና ተቋማት ወደስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ቤት ለመገንባት እንደማያንሱ በተጨባጭ ያሳየ ነው፡፡
አሁንም ይቀጥላል፡፡ በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን ከተሞቻቸውን መልሰው ይገነባሉ፡፡ ተቋማት ወደቀደመ ቁመናቸው ይመለሳሉ፡፡ በሃዘን የተሰበሩ ቤቶችን ስብራታቸውን እጅ ለእጅ ተያይዘን መጠገን ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡
አሁን አንገብጋቢው ጉዳይ በህወሃት የሽብር ቡድን የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋምና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ያለውን ህዝብ መታደግ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትገነባው በኢትዮጵያውያን ነው፡፡ ቤታችንን በራሳችን እጅ እንገነባለን፡፡

Leave a Reply