You are currently viewing ኢትዮጵያ እየተዋጋች ያለችው…

ኢትዮጵያ እየተዋጋች ያለችው…

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ እየተዋጋች ያለችው አሸባሪነትን ነው። አሸባሪነትን የምትዋጋው ደግሞ የህዝቦቿን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ነው።አሸባሪነት በባህርይው ሀገር አፍራሽ ድርጊት ነው፤አሸባሪነት የተረጋጋ ሀገርና ሰላሙ የተጠበቀ ህዝብን ማየት አይመኝም።
ሀገር የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኗ ዋጋዋ እጅግ ውድ ነው። የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ የህዝቦችን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በዘላቂ መልኩ ለማስቀጠል ብዙ መስዋዕቶችን መክፈል የግድ ይላል። ኢትዮጵያም እየተዋጋች ያለችው እነዚህን መሰረታዊ የህልውና ጉዳዮቿን ሊያሳጧት ከሚሯሯጡ ሃይሎች እና ሰላምን ከማይፈልጉ ሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ነው።
 
እናት ሀገራቸውን ማቁሰል፣ የራሳቸውን ፍላጎት ማርካት፣ መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ፣ ተቋማትን ማበላሸት በወረራ በያዟቸው አካባቢዎች የፈፀሟቸው ተግባራት ማሳያ ነው። ይህ ሁሉ ግፍና በደል በግልፅ የታያቸው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለዚህ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳና ግብረ አበሮቹ የማያዳግም መልስ በመስጠት ላይ ናቸው።
 
የአሸባሪው ህወኃት ሂሳብ የማወራረድ የበቀል ብትር ያረፈባቸው የአማራ እና አፋር ክልሎች ከሌሎች ክልሎች ጋር በአንድነት በመተባበር እና በኅብረት በመደራጀት አካባቢያቸውን ነፃ ማውጣት እየቻሉ ነው። ይህም ሀገር የማተራመስ የውጭ ተልዕኮ በዚህ ትውልድ እንደሚቀለበስ ያረጋገጠ ነው።
 
የአባቶቹን አደራ በተረከበው በዚህ ትውልድ ሀገር አፍራሾች ይፈርሳሉ፤ የሀገራችን ሉዓላዊነትም አይደፈርም።ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆነው በህልውና ጦርነቱ ሁላችንም ዘማቾች ስንሆን ብቻ ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ