You are currently viewing ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ተላለፈ

ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ተላለፈ

  • Post comments:0 Comments
ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ተላለፈ
ብልጽግና ፓርቲ(ህዳር 25/2014) ከአሸባሪው ህወኃት ጋር ፊት ለፊት በመፋለም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡
በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ አህመድ አሸባሪው ህወኃት በአፋር ክልል በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን ማድረሱን ጠቅሰው በጥቅምት ወር በተካሄደ ዳሰሳዊ ጥናት መሰረት አፋጣኝ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውና ጥቃቱ በደረሰባቸው ወረዳዎች የተፈናቀሉ ከ360ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ሰብሳቢዋ አያይዘውም የሽብር ቡድኑ ጥቃት ባደረሰባቸው አካባቢዎች የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከጥቅም ውጭ ማድረጉን አውስተው ጥቃት በደረሰባቸው 21 ወረዳዎች ከ1.3 ሚሊዬን በላይ የክልሉ ህዝብ የኢትዮጵያን ህዝብ አስቸኳይ ድጋፍ ይፈልጋል ያሉ ሲሆን የአርብቶ አደሩ ሀብትና ንብረት በአሸባሪው ህወኃት ቡድን ከመዘረፉም በላይ እንስሳትን በመግደል የጭካኔ ተግባሩን አሳይቷል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልግ አካል አዋሬ አካባቢ በሚገኘው ሱልጣን አሊ ሚራህ መስጂድ ቅጥር ግቢ በመገኘት መለገስ የሚቻል ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000444559512 ገቢ ማድረግ እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡

ምላሽ ይስጡ