በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ለመላው ጥቁር ህዝብ ምሳሌ የሚሆን ታሪክ ይጻፋል፤  በሚራክል እውነቱ

በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ለመላው ጥቁር ህዝብ ምሳሌ የሚሆን ታሪክ ይጻፋል፤ በሚራክል እውነቱ

  • Post comments:0 Comments

ከምስረታው ጀምሮ በህዝብ ደም ስልጣን፤ በህዝብ ጉልበትና ላብ የግል ጥቅምን ማካበት፤ በነጻነት የኖረን ህዝብን በባርነት መግዛት፣ አገር የሁሉ ሁና ሳለች አንደኛው ልጅ ሌላኛው የእንጀራ ልጅ ሆነው እንዲኖሩ የፈረደባቸው የጥፋት ቡድኑ ህወኃት በጥቂት ሰዎች በጫካ ተጠንስሶ ከተወለደ ጀምሮ በበታችነት ስሜት ውስጥ ሆኖ የበላይ ለመሆን ሲል በንጹሐን ደም ላይ ተረማምዶ የስልጣን ማማን ለመቆናጠጥ የበቃ የወንበዴዎች ስብስብ ነበር፡፡

ስልጣኑን በህዝብ ድምጽ ሳይሆን በጉልበቱ ያገኘው አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለህዝብ ምንም አይነት ክብር ሳይኖረውና የአገር ፍቅር ስሜት ሳይኖረው ኢትዮጵያን ለ27 ዓመታት በግፍና በጸረ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ከፋፍሎ የገዛ የለየለት የሽብር ቡድን ነው።

በዚህ መንገድ ወደ ስልጣን የመጣው የሽብር ቡድኑ ህወኃት አገሪቱ ያላትን ሀብትና ንብረት በመዝረፍ የውንብድና ስራውን በገሃድ አሳይቷል፡፡ይሁን እንጂ በህዝብ ደም የተገኘው ስልጣን ለኢትዮጵያ የሚመጥን፤ ለኢትዮጵያውያንም የሚበጅ አልነበረምና ኢትዮጵያዊያን ልዩነትን አንሻም፤ ባርነት በቅቶናል፤ ዴሞክራሲ ያስፈልገናል፤ ህብረ ብሔራዊነት መለያችን ነውና ይከበርልን፤ ወንድማማችነታችን ለአገር ብልጽግና መሰረት በመሆኑ የልዩነት ግንቡን አፍረሰን ድልድዩን መገንባት እንፈልጋለን በማለታቸው በህዝብ ግፊት ከአራት ኪሎው የስልጣን ዙፋኑ ተነሳ፡፡ይህ የህዝብ ታሪካዊ ውሳኔ በደማቅ የታሪክ መዝገብ ተከትቦ ይኖራል፡፡

በብዙ ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት የተገነባች አገር ኢትዮጵያን ቀስ በቀስ ደሟን በመምጠጥና በማቀጨጭ ብሔርተኝነትን ከምንጊዜውም በላይ እንዲገን በማድረግ ልዩነትን እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል። ሆኖም የኢትዮጵያ ታላቅነት፤ የኢትዮጵያዊነትም ገናና ስነልቡና፤ የኢትዮጵያውያን ህብረትና አንድነት መቼም ይሄን ዓይነት ሴራ ስለማይፈቅድ፤ በህዝብ ደም የሰከረው አሸባሪው ቡድን ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ባደረሰው ግፍ ምክንያት ከስልጣን መንበሩ በውርደት እንዲወርድ ሆኗል።

በዚህ ያኮረፈው አሸባሪው የትህነግ ቡድን መቀመጫውን መቀሌ በማድረግ አገራዊ የክህደት  ጅማሮውን በሰራዊታችን ላይ ጥቃት በማድረስ አሳዬ፤ በዚህም ሳያበቃ በአማራና በአፋር ክልሎች ዘልቆ በመግባት ንጹሃንን በጅምላ በመረሸን አሸባሪነቱን በገሃድ አስመሰከረ፡፡ የሽብር ቡድኑ ከውልደቱ ጀምሮ አሁን እስካለበት የቁልቁለት ጉዞ በጥፋት የተሞላ አካሄድ እየተከተለ ይገኛል፡፡

ይህ የመላው ኢትዮጵያዊያን ነቀርሳ የሆነውን የሽብር ቡድን ዳግም ላይመለስ እስከወዲያኛው ለመሸኘት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሆ ብለው ከጫፍ ጫፍ ተነስተዋል፡፡የጋራ ጠላታችን የሆነውን ህወኃት በጋራ በመደምሰስ ኢትዮጵያም ሰላሟን እንድታገኝ ኢትዮጵያዊያንም የሰላም አየር እንዲተነፍሱ እንዲሁም ከጠላት ጋር አብረው እየሰሩ ላሉ አካላት ኢትዮጵያን ማንበርከክም ሆነ ማሸነፍ እንደማይቻል ትምህርት እንዲወስዱበት ያስችላል፡፡

ዛሬ ከጠላት ጋር እያደረግን ያለነው ትግል ለኢትዮጵያ ነጻነት ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር አፍሪካዊያን ስለመሆኑ በርካቶች ምስክርነታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ኢትዮጵያ የመላውን ጥቁር ሕዝብ ትግል እያካሄደች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ነጻነቷ ተጠብቆ፣ ሉዓላዊነቷ ተከብሮ ዛሬ ላይ የደረሰችው ላለፉት ዘመናት በምዕራባዊያን ሲደርስባት የነበረውን ጫና መቋቋም በመቻሏ ነው፤ የኋላ ታሪኳ የሚያስረዳውም ይህንኑ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ነጻነቷን ከማንም በፊት ለዘመናት አውጃ መኖር የቻለች አገር ነች፤ ስለ ነጻነት፣ ስለ አገር ፍቅርና ክብር፣ ስለጀግንነትና ጫናን ተቋቁሞ ራስን ስለማስከበር ከማንም በፊት እናውቀዋለን፣ አስረጂ አንፈልግም፡፡ እንደ አገር የገጠመንን አሁናዊ ችግር በራሳችን አቅም መፍታት የምንችለው በመሆኑ ምንም አይነት የውጭ ጣልቃ ገብነት ፈጽሞ ቦታ የለውም፡፡

በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ፍጹም ከእውነት የራቁ፤ የተዛቡና አሳሳች መረጃዎችን ያለ ከልካይ ሲያሰራጩ ይስተዋላል፡፡ ዴንማርካዊው የፖለቲካ ምሁር ፕሮፌሰር ቶቢያስ ሃግማን ምዕራባዊያን በሚዘውሯቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን እውነታ በተሳሳተ መልኩ ስለማቅረባቸው ይናገራሉ።

ፕሮፌሰሩ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራውንና ከፍተኛ ሕዝባዊ ቅቡልነት ያለውን መንግሥት ለማንኳሰስ የማጠልሸት ሥራ እየሰሩ መሆኑን በአጽንኦት የተናገሩ ሲሆን እነዚህ አገራት ከዚህ አፍራሽ አካሄዳቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም “ትግሉ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው” ኢትዮጵያን አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው” ማለታቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የምዕራባዊያን አገራት ፍላጎት ማሳኪያ መንገዶች መሆናቸውን በግልጽ የሚያስረዳና የበርካቶች ጣልቃ ገብነት መኖሩን ያመላከተ ነው፡፡

ከጠላት ጋር እያካሄድነው ያለነው መራር ትግል ከኢትዮጵያ ባለፈ ለመላው የጥቁር ሕዝቦች ነጻነት መሆኑን መረዳትና ከኢትዮጵያ ጎን መቆም ብልህነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ “ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ በማለት ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ መላው አፍሪካዊያንን ከማነሳሳቱም ባሻገር አንዳንድ የምዕራባዊያን አገራት ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ እያደረሱት ያለውን ጫና ነገ በሌሎቹ የአፍሪካ አገራት መድረሱ ስለማይቀር ትግሉ አህጉራዊ ይዘት እንዲኖረው ያስችላል፡፡ይህም አፍሪካዊያን በአንድነት ተነስተው የእጅ አዙር ቅኝ ግዛትን መከላከል ያስችላቸዋል፡፡

Leave a Reply