You are currently viewing ትህነግ በኢትዮጵያ ላይ…

ትህነግ በኢትዮጵያ ላይ…

  • Post comments:0 Comments

ትህነግ በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ጦርነት ካወጀ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም ዓመት አለፈው፡፡መንግስት ኢትዮጵያን ሊያፈርስ ከመጣው የሽብር ቡድን ጋር ነው እየተዋጋች ያለችው።ጦርነት በከፈተብን የሽብር ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተሰጠ ያለው ይህ የሽብር ቡድን መደበኛ ስራ አድርጎ የያዘው ህዝብን በሐሰት ወሬ ማሸበር፣የውንብድና ስራ መስራት፣መግደልና መድፈር በመሆኑ ለማንም የማይጠቅም የአሮጌ ዘመን አስተሳሰብን የተሸከመ በአዲስ ምዕራፍ ላይ ለምትገኘው አገራችን ፋይዳ ቢስና ከብልጽግና መስመራችን ሊያደናቅፈን የሚችል እንቅፋት ስለሆነ ነው፡፡

የመላው ኢትዮጵያዊያን ጠላት ከሆነው ትህነግ ጋር እየጠገምን ያለነው ጦርነት ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ መሆኑን ነው። የትህነግ ዓላማ አንድና አንድ ነው፤የሽብር ቡድኑ ባህሪ ሀገርን ማፈራረስና ህዝቦቿን መበታተን ነው፡፡ዓለም ላይ ይህ እንዲሆን የሚፈቅድ አንዳች አገር የለም፤በአንጻሩ ኢትዮጵያ ራሷን ከአሸባሪው ህወኃት ለመከላከልና ዳግም ስጋት እንዳይሆን እየወሰደች ያለውን እርምጃ ተቃውመው ሲቆሙ አይተናል፡፡

ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል አሸባሪው የህወኃት ቡድን በድጋሜ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር ከቶም አይችልም፡፡ አገሩን ለአሸባሪው ቡድን አሳልፎ የሚሰጥ ኢትዮጵያዊ የለም፤የትኛውንም መስዋዕትነት ተከፍሎም ቢሆን ኢትዮጵያ ህልውናዋ እንደተጠበቀ ትኖራለች፤ሀገር የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኗ ዋጋዋ እጅግ ውድ መሆኑን የተረዱት ኢትዮጵያዊያ ከሰራዊታችን ጎን ሆነው ጠላትን ፊት ለፊት እየተፋለሙት ይገኛሉ።

ነጻነት በብዙ መስዋዕትነት የሚገኝ መሆኑን ለማናችንም የተደበቀ አይደለም፡፡የጋራ ሰላምና ደህንነታችንን ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች በዘላቂ መልኩ ለማስቀጠል ብዙ መስዋዕቶችን መክፈል የግድ ይላል። ለዛም ነው እነዚህን መሰረታዊ ጉዳዮችን ሊያሳጡን ከሚሹ የሽብር ቡድን ሀይሎች ጋርፊት ለፊት እየገጠመን ያለነው፡፡

ምላሽ ይስጡ