አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ በአዲስ አበባ ደግሰውት የነበረው የጥፋት ሴራ መክሸፉ ተገለጸ

አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ በአዲስ አበባ ደግሰውት የነበረው የጥፋት ሴራ መክሸፉ ተገለጸ

  • Post comments:0 Comments
አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ በአዲስ አበባ ደግሰውት የነበረው የጥፋት ሴራ መክሸፉ ተገለጸ
አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ በአዲስ አበባ ደግሰውት የነበረው የጥፋት ሴራ መክሸፉን የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን በርካታ የወንጀል ምርመራ ተግባር መከናወኑን በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ነጋሽ በጋራ በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል።
በመግለጫውም አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ደግሰውት የነበረው የጥፋት ሴራ መክሸፉን አስታውቀዋል።
ለሽብር ቡድኑ የጥፋት ተልእኮ ማስፈጸሚያ ሊውሉ የነበሩ የቡድን የነብስ ወከፍ መሳሪያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሃገሪቱ ዋና ከተሞች የተለያዩ ሁከትና የሽብር አመጽ በማነሳሳት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገው ጥረት ከሽፏል ተብሏል።
በተለይሞ በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ የአሸባሪው ተላላኪዎች እስከ ጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
እንደ አሚኔ ዘገባ አንዳንድ ስነ ምግባር የጎደላቸው የጸጥታ ኃይሎች ከ3000 እስከ 50 ሺሕ ብር እጅ መንሻ በመጠየቅ ከአጥፊዎች ጋር ተባባሪ የነበሩ በሃገር ወዳድ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Leave a Reply