You are currently viewing ሕዝብን በብሔር፣በሐይማኖትና…

ሕዝብን በብሔር፣በሐይማኖትና…

  • Post comments:0 Comments
#Prosperity party
ሕዝብን በብሔር፣በሐይማኖትና በጎሳ በመልፋፈል የአራት ኪሎውን ስልጣን ማራዘም የሽብር ቡድኑ ትህነግ መለያ ነበር። ትናንት ምንም በማያውቁ በተከፈለ የንጹሃን ደም ከጫካ ወጥቶ ወደ ስልጣን መጣ፤ስልጣን ከያዘበት ጊዜም ጀምሮ ከህዝብና ከአገር ጥቅም ይልቅ የጥቂቶችን ጥቅም የሚያስከብር ስርዓት በመፍጠር የመሪዎቹን ኪስ አደለበ፣ በህዝብ ላይ በሚያሳየው የፀረ ዴሞክራሲያዊነት አገዛዝና በሚያደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የስልጣን ዘመኑ ከፍ እንዲል አድርጎት ቆይቷል።
 
ትናንት ሲፈጽም የነበረው ግፍና በደል አልበቃ ብሎት፤ የሙጥኝ ካለው ስልጣን በህዝብ ግፊት ወርዶ እንኳ ዛሬም እንደትናንቱ ህዝብን በሀሰት ወሬዎች ማሸበር፣የናፈቀውን ስልጣን መልሶ ለማግኘት ንጹሃንን መግደል፣ከተሞችን ማፍረስና መዝረፍ ውስጥ ይገኛል፡፡ከትናንቱ ስህተት ያልተማረ ፤ታጥቦ ጭቃ ይባል የለ።
 
የአሸባሪው ህወኃት ቡድን አዲስ አበባን ለቆ መቀሌ ከገባ በኋላ ሰላም ኢትዮጵያ ውስጥ ጠፍቷል፤ በተፈጠረው አገራዊ ለውጥ ክፉኛ የተበሳጨው ትህነግ ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ከፊቱ ያገኘውን ነገር ሁሉ ከጥቅም ውጭ በማድረግ ስራ ውስጥ ተጠምዷል።ባሳለፍነው አንድ ዓመት እንኳን የቡድኑ የጭካኔ በትር ያላረፈበት የማህበረሰብ ክፍል የለም ማለት ይቻላል።
 
አገራችን በታሪክ በዚህ የሽብር ቡድን እንደደረሰባት አይነት ግፍና በደል ደርሶባት አያውቅም።ዓለም ላይ መልካም ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው በጭካኔ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎች እንዳሉም ይታወቃል።ሆኖም ግን እንደ ትህነግ አይነት ሲያስተዳድረው የነበረውን ህዝብና ሲመራት የነበረችውን አገር በሚዘገንን መንገድ ጥቃት ማድረስ በየትኛውም ዓለም አልታየም።

ምላሽ ይስጡ