በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ አዲሱን የአሜሪካ መንግስት መግለጫ አስመልክቶ ከVOA ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ሀሳቦች፡-

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ አዲሱን የአሜሪካ መንግስት መግለጫ አስመልክቶ ከVOA ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ሀሳቦች፡-

  • Post comments:0 Comments
በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ አዲሱን የአሜሪካ መንግስት መግለጫ አስመልክቶ ከVOA ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ሀሳቦች፡-
*********************************************************************
• ኢትዮጵያን ማገዝ የሚቻለው አሸባሪነት እና ጥፋተኝነት እንዲወገድ የሚያደርግ እገዛ እንጂ እጅን አስረዝሞ ባልተገባ ሁኔታ ጣልቃ ለመግባት መሞከር ተገቢ ነው ብለን አናምንም፡፡
 
• አሜሪካ ከጅምሩ ጀምሮ ህወኃትን አስመልክቶ እውነታውን ከመረዳትና በመረጃ ላይ ተመስርቶ ተገቢ አቋም ከመያዝ አንጻር ትክክለኛ አቅጣጫ እየከተለች ነው ብለን አናምንም እንደ ኢትዮጵያ መንግስት፡፡
 
• ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነሳን ቡድንና አንድ መቶ አስራ አምስት ሚሊዬን ያህል ህዝብ የሚያስተዳድረውን የኢትዮጵያ መንግስት እኩል አይቶ ማዕቀብ የሚመስል ውሳኔ ማሳለፍ ታሪካዊ ስህተት እና ቆም ብሎ ማሰብ እንደሚያስፈልግ ነው የምናስበው፡፡
 
• አሜሪካ ከአልቃይዳ ወይም ከአይ ኤስ አይ ኤስ ጋር ወይም ከሌሎች የሽብር ቡድኖች ጋር ቁጭ ብላ ተደራድራ ችግሩን ለመፍታት የሞከረችበትን አጋጣሚ ማየት ነው የናፈቀኝ፡፡ ራሷ የማታደርገውን ነገር ለሌሎች አካላት መመኘት ተገቢ አይደለም፡፡
 
• ኢትዮጵያ የምትበታተንበትን 86 ገጽ አዘጋጅቶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ቡድን ጋር ቁጭ ብላችሁ ተደራደሩ ማለት ስህተት ነው ብለን ነው የምናስበው፡፡ ኢትዮጵያ መበተን አለባት ይላል፤ የስትራቴጂው ቁጥር አንድ ፖለቲካዊ ጥቃት እንሰነዝራለን ይላል፡፡ የስትራቴጂው ቁጥር ሁለት በኢትዮጵያ ውስጥ አመጾች፣ ብጥብጦችና ግጭቶችን እዚህም እዛም እንቀሰቅሳለን ይላል፡፡ ሶስተኛው ስትራቴጂ በተነሳሽነት መከላከያ ሰራዊቱን እንመታለን ይላል፡፡ ይሄን አሜሪካ ትገነዘባለች ብለን ነው የምናስበው፡፡ ከዚህ ቡድን ጋር ቁጭ ብላችሁ ተደራደሩ የሚለው አስተሳሰብ እጅግ በጣም የተሳሳተ ነው፡፡
 
• ድርድር ብንቀመጥ እንኳ ለማደናገሪያ ስትራቴጂ ነው ብሎ ጽፎ ወደ ስራ ከገባ አካል ጋር መወያየት የኢትዮጵያን ችግር ይፈታል ብለን አናምንም፡፡ የራስን አቅም በራስ መገንባትና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በራስ አቅም የመፍታት ስራ የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ብሎ አቅዶ እየሰራ ነው የሚገኘው፡፡
 
• ጫናዎችና ችግሮች ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ዘላቂ የሚሆነው የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊ አንድነት አስጠብቆ የውስጥ የኢኮኖሚ አቅምን አጎልብቶ ለውጭ ጫናዎች የማይንበረከክ የውስጥ የኢኮኖሚ ስትራቴጂ መገንባት ስለሆነ በዚህ ላይ እየተረባርብን እንገኛለን፡፡ ከድህነት በዘላቂነት ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ማስቀጠል ነው ያለብን፡፡

Leave a Reply