የህዳሴ ግድብን ጨርሰን…

የህዳሴ ግድብን ጨርሰን…

  • Post comments:0 Comments
የህዳሴ ግድብን ጨርሰን የምንደሰትበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለአባይ ግድባችን መሳካት የበኩሉን በማድረግ ከዚህ ትውልድ መካከል ስሙን በወርቅ ቀለም መጻፍ አለበት። ለሀገራችን መልካም ለመሥራት ምርጡ ጊዜ ላይ ነን። ሀገራችንን እንወዳለን የምንል ከንግግር ባለፈ በተግባር የምንፈተንበት የደስታና የጭንቅ ወቅት ላይ ነን። አባይ የእኔና የእናንተ የህብረት ውጤት ነው።
ተያይዘንና ተደጋግፈን እዚህ አድርሰንዋል አሁንም በአንድነት ፍጻሜውን እናይ ዘንድ አንድ ሆነን መቆም ግድ ይለናል። በአለንበት ዘመን ላይ ለአባቶቻችን ክብርና ስም ለእኛም ለሚመጣውም ትውልድ ባጠቃላይ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብርሀናዊ ነገ ስንል አባይን ገድበን የከሰርንውን ትላንትና በልማትና በብልጽግና መመለስ አለብን እላለሁ። ይሄ የሁላችሁም ሃሳበን እንደሚሆን አልጠራጠርም። ምክንያቱም ድህነት መሮናል፣ ማጣት በቃን ብለን የተነሳንበት ጊዜ ስለሆነም ነው።
የዛሬ ሰዎች ነን ለሀገራችን አስፈላጊ የምትሆንበት ወቅት ዛሬ ነው። ለሀገርም ሆነ ለትውልድ ብርሃን የምንሆንበት ጊዜ ላይ እንገኛለን.. ብርሃናችንን በጋራ እናብራ። ዓደዋ በአባቶቻችን አንድነት የተጻፈ የእያንዳንዳችን ታሪክ ነው።
ዓድዋ ህብረት የወለደው የኢትዮጵያዊያን የክብር ጥግ ነው። እኛም ከሁለተኛው ዓድዋ ጋር ግብ ግብ ውስጥ ነን። ሁለተኛውን ዓደዋ በድል ልናጠናቅቅ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።

Leave a Reply