ከሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ እንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ

ከሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ እንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ

  • Post comments:0 Comments
ከሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ እንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ሀገር አቀፍ የምርጫ ውጤት ማምሻዉን ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ሱማሌ ክልል በተወካዮች ምክርቤት ካለው 23 ወንበር ብልፅግና ፓርቲ 23ቱንም አሸንፏል ።
የክልሉ ምክር ቤት ካሉት 272 ወንበሮችም 262ቱን ወንበር ብልፅግና ፓርቲ ማሸነፉን በቦርዱ የተገለጸው ውጤት ያመለክታል፡፡
መንግሥት እና ሕዝብ በጋራ ባደረጉት ዘርፈብዙ ጥረት 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ከተካሄዱ ምርጫዎች ፍፁም በተለየ ሁኔታ ነፃ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያተረፈ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል።
በዚህ ምርጫ ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ከመጣሉም ባሻገር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ለዲሞክራሲ ያላቸው ቀናኢነት በተግባር መታየት ችሏል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ አዲስ ምእራፍ እንዲከፈት በቁርጠኝነት እየሰራ ያለው ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ከድህነት ወደ ብልፅግና ማሸጋገር ይችላል በሚል እምነት ድምፃችሁን ለሰጣችሁን የክልላችን ነዋሪዎች እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ለደከማችሁ
የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ለተገኘዉ ውጤት የናንተ አስተዋጽኦ በምንም የማይተካ በመሆኑ የሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ የላቀ ምስጋውን ያቀርባል።
ብልፅግና ፓርቲ በሕዝብ የተሰጠውን ሀላፊነት አክብሮ በመቀበል በቀጣዮቹ አመታት በሱማሌ ክልል ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ምድር ብልፅግና እንዲረጋገጥ በእውቀትና በእውነት ጠንክሮ ለመስራት የተዘጋጀ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጣል።
ብልፅግና ፓርቲ
ምርጫው ሰላማዊ ነፃና ፍትሃዊ እንዲሁም በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን አስተዋጽኦ ላባረከቱ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት በተለይም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ያለውን የላቀ አድናቆትና ምስጋና ይገልጻል ።
በመጨረሻም በአጠቃላይ በመራጭነት ለተሳተፋችሁ ለክልላችን ነዋሪዎች በተለይ ደግሞ
ድምፃችሁን ለፓርቲያችን ለሰጣችሁ መራጮች በሙሉ በድጋሚ ምስጋናችንን እየገለፅን
እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን እንላለን።
የሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ
ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም
ጂግጂጋ

Leave a Reply