ባህሬን ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ሪፎርም እንደምትደግፍ ገለጸች

ባህሬን ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ሪፎርም እንደምትደግፍ ገለጸች

  • Post comments:0 Comments

ባህሬን ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ሪፎርም እንደምትደግፍ ገለጸች

ባህሬን ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ሪፎርም እንደምትደግፍ የባህሬን የገንዘብና የብሔራዊ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ በኢትዮጵያ ህዝቦች ይሁንታ ያገኛው ዲሞክራሲያዊ መንግስት ምስረታ በጥሩ ሁኔታ በመጠናቃቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ለአቻቸው አቶ አህመድ ሺዴ የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው በድጋሜ በመሾማቸው የደስታ መልዕከት አስተላልፈዋል።

በባህሬን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት መሪ አምባሳደር ጀማል በከር ጋር የሁለትዮች የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ትብብር በሚጠናከርበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሪፎርም ሀገሪቱ ጠንካራና ክልላዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናክር ዋነኛ ፖሊሲ በመሆኑ የባህሬን መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለባህሬን ኢኮኖሚ እድገትና ቀጣይነት እያበረከቱ ያለውን ሚና አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር በአገራችን እያተካሄደ ያለውን ሪፎርም በተለይም የክልላዊ ውህዳትና ትብብር እንዲሁም ከመካከለኛም ምስራቅ ጋር ያላንን ትብብር ለማጠናከር የሚረዱ ዘርፋ ብዙ እንቅስቃሴ እያተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ አገራችን አገር አቀፍ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ነድፋ እየሰራች መሆኑን በተለይም በዚህ በአለም አቀፍ የኮቪድ-19 ወራርሽኝ ወቅት አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ መንገራገጭ የገጠመውን ፈተናዎች በመቋቋም፤ዠ፤ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማነቆ የሆኑትን የህግና የአሰራር በመፈተሽ ለኢንቨስተሮች የተመቻች አገር እንድትሆን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም አገራችን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ፕራይቬታይዝ የማድረግ ፤ የተለያዩ የአግሮ ፕሮሰስንግ፤ ማንፋክቻሪንግ፤ የአይ.ሲቲ.ና የቱሪዝም ሴክተሮችን በልዩ ሁኔታ ድጋፍ በማድረጓና ጥሩ አመራር በመሰጠቱ ይበልጥ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በቀጣይ የሁለቱ ወንድማማች አገራት ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ በሚጠናከርበት ዙሪያ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገነነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply