You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ለተሾሙ ከፍተኛ መራሮች ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ለተሾሙ ከፍተኛ መራሮች ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

  • Post comments:0 Comments

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ለተሾሙ ከፍተኛ መራሮች ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

********************************************************************************************

ኢትዮጵያን ማገልገል ዕድል ነው፣ምክንያቱም ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለበት አገር መቶ የምንሞላ ሰዎች ስንመረጥ ከአንድ ሚሊዮን ሰው ተመርጠህ የወጣህ አንድ ሰው ነህ ማለት ነው፤ከ1 ሚሊዬን ሰው ስለምበልጥ ነው የሚል የተሳሳተ ግምት እንዳይዛሁ አደራ፤ዕድል ያጡ ግን ብቃት ያላቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ መውደድም መጥላትም አሳምሮ ያውቃል፤ሲወድ በአንቀልባ ይሸከመናል፣ትክሻው ላይ ያወጣናል፣ራሱ ላይ ያወጣናል የሚያስቀምጠን ቦታ ነው የሚቸገረው፤ከፍቅሩ ብዛት፡፡አንቅሮ ሲተፋም ይተፋል፤ሲጠላም ይጠላል፡፡

የሚያስፈልገውና ጥንቃቄ የሚሻው ጉዳይ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅርና አክብሮት አትለማመዱት፤ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም በርካታ ሰዎች ተኮፍሰው በተለያዬ ኃላፊነት የመሩ ሰዎች አሉ፤ኢትዮጵያ መውደድና ማክበር ብቻ ሳይሆን የተኮፈንም ማስተንፈስ ስለምትችል ብዙዎቹ ተንፍሰዋል፡፡በመኮፈስ መከበር፣በመኮፈስ በአጃቢ ጋጋታ የምናስብ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው ቀስ ብሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ያስተነፍሳል፤ብዙዎች ላይ ሆኗል እኛም ላይ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

ኢትዮጵያን ለመቀየር ሰማይ እንድትቧጥጡ አይጠበቅም፤የሌለ ነገር እንድታመጡ አይጠበቅም፤ያለውን ነገር በጥልቀት አይታችሁ ተከታዮቻችሁ ደግሞ እንዲያዩ አድርጋችሁ ማውጣት ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያሉ ሃብቶች አቧራ ለብሰዋል፤አቧራ የለበሱ ቋጥኝ የተጫነባቸው፣በየስፍራው የሚታዩ አረሞች ሙጃዎች የበቀለባቸው የሚያስደንቁ ሃብቶች አሉ፡፡ሙጃውን ነቅለን፣አረሙን ነቅለን፣አቧራውን አራግፈን እነዛን የሚያብረቀርቁ የብልጽግና መሰረቶች ማውጣት መቻል ነው የእኛ ስራ የሚሆነው፡፡

ባለስልጣን መሆን ሳይሆን ሰው መሆን ያሥፈልጋል፤ሰው ሆነን ሰውን ለማንሳት ከተጋን ይሳካልናል፡፡ባለስልጣን ሆነን ላይ ተቀምጠን ወደ ላይ ልንጎትት ከሆነ ግን አስቡት እኛ 100 ነን የሚጎተተው ግን መቶ ሚሊዮን ነው፤እኛ ወደ እሱ እንጂ እሱ ወደ እኛ ልናመጣው አንችልም፤ይከብዳል፡፡

ሰው ሆነን ሳንሳፈፍ አብረን አንድ እርምጃ እየመራን ሁለት እርምጃ እየተከተልን ከሄድን ግን ተያይዘን መውጣት እንችላለን፡፡ተያይዘን ለመውጣት እንድንችል ከዚህ ዕድለኛ ቡድን የሚጠበቀው እንደ ግልም እንደ ቡድም በጠራ ግብ ሰው ሆኖ መትጋት መቻል ነው፤ያንን ካመጣን ውጤቱ ከደጃችን ነው፤ይገኛል፣ይጨበጣል፣ይታያል፡፡

ለምሳሌ እኔን ብትወስዱ መቀለድ አልፈልግም፤የተሰጠችኝኝ ካርድ በጣም መጠቀም እፈልጋለሁ፤ባለፉት ሶስት ዓመታት እንደነበረው አይነት ጨዋታ ማስተናገድ አልፈልግም፡፡ አሁን ለዚህ ራዕይ እና ዓላማ የተሰጠ ሰው ካለ በህብረት መስራት ካልፈለገ መንገድ መልቀቅ ብቻ ነው፤እንጂ ከእንትን ሰፈር ስለመጣሁ፣ሐይማኖቴ እንትን ስለሆነ፣ፌስ ቡክ አርበኞች ስላሉኝ አይሰራም፤እሱ ባለፈው ሶስት ዓመት አልቋል፡፡

ይህንን ካርድ ማባከን ማለት የሚጻፈው ቼክ ላይ ስርዝ ድርዝ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ቼኩ እንዳይሰራ ማድረግ ማለት ነው፤ለዚያ እኔ ፈቃደኛ አይደለሁም፤እናንተም ፈቃደኛ ትሆናላችሁ ብዬ አላስብም፡፡

ምላሽ ይስጡ