የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰንደቅ ዓላማ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰንደቅ ዓላማ

  • Post comments:0 Comments
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ሰንደቅ ዓላማችን ተገቢውን ክብርና ቦታ እንዲያገኝ ከተደረጉ ጥረቶች አንዱ፤የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን በየዓመቱ ማክበር ነው። የበዓሉ መከበር ሰንደቅ ዓላማችንን እንዴት ማክበር እንዳለብን ግንዛቤ ከመፍጠሩም ባሻገር፤ ለሰንደቅ ዓላማችን ተገቢውን ቦታ ለመስጠት ጠቃሚ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አይካድም። ይሁን እንጂ በበዓሉ ምክንያት እዋጁ ይበልጥ ሲጣስ ማየት ደግሞ ለበለጠ ትዝብት የሚዳርግ ነው።
በተለይ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በንግድ ደርጅቶች በራፍ ላይ የሚሰቀሉት ሰንደቅ ዓላማዎች የቆሸሹ፣ የተቀዳደዱና ቀለማቸው በጉልህ የማያስታውቅ ናቸው። ብዙዎቹም ዓላማውን በመረዳት ሳይሆን ለግብር ይውጣ የተሰቀሉ ይመስላሉ።
የሰንደቅ ዓላማ አዋጁ የሰንደቅ አላማው ቀለማት ብሩህ እና መሰረታዊ መሆን እንዳለባቸው ይደነግጋል። የሰንደቅ ዓላማው ወርድ የቁመቱ እጥፍ መሆን ይኖርበታል። ይሁን እንጂ በዝናብ፣በፀሐይ፣በንፋስ፣ በአቧራና በእርጅና ምክንያት ቀለማቸው የፈዘዘና የተቀደዱ እንዲሁም መጠናቸው ከአዋጁ የሚቃረን ሰንደቅ ዓላማዎችን በተለያዩ ቦታዎች ማየቱ የተለመደ ሆኗል። ትክክለኛውን ቀለምና መጠን አለመጠቀም በአንቀፅ 23(3) መሰረት የተከለከለና ለግለሰቦች እስከ 3ሺ ብር ለድርጅቶች ደግሞ እስከ 6ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ ወይም አንድ ዓመት ከስድስት ወር በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነም ተደንግጓል።

Leave a Reply