You are currently viewing ይች ሰንደቅ አላማ…

ይች ሰንደቅ አላማ…

  • Post comments:0 Comments
ይች ሰንደቅ አላማ እልፍ አላፍ ጀግኖች ለክብሯ የተዋደቁላት፤የቀደምት ስልጣኔ መልክት የሆነች፤የአፍሪካ /የጥቁር ህዝብ ነጻነት ምልክት፤የአይበገሬነትና አልደፈር ባይነት አርማ ፤በብዝሃነት ያጌጠችና መልከ ብዙ፤ ግን አንድ ታላቅ አገር የተወከለችበት፤ጥንታዊና ታሪካዊ አገር እንዲሁም ባለብዙ ጥበብና ታሪክ ትልቅ ህዝብ የሚወከልበት ሰንደቅ አላማ ናትና ከፍ ከፍ ትበል፡፡
ዛሬ 14ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን “በአዲስ ምዕራፍ፤ በተሟላ ሉዓላዊነት፤ ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ነውና ሁላችንም ባለንበት ለዚህች ባለዝና ሰንደቅ አላማ ክብር እንስጣት፡፡

ምላሽ ይስጡ