You are currently viewing “የውጭ ጣልቃ ገብነት ፍላጎቱ እየጨመረ ቢሆንም እየተሳካላቸው አይደለም” – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

“የውጭ ጣልቃ ገብነት ፍላጎቱ እየጨመረ ቢሆንም እየተሳካላቸው አይደለም” – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

  • Post comments:0 Comments
“የውጭ ጣልቃ ገብነት ፍላጎቱ እየጨመረ ቢሆንም እየተሳካላቸው አይደለም” – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እየጨመረ ቢሆንም፤ እየተሳካላቸው እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮች የተደረገው የጣልቃ ገብነት አዝማሚያ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በኢትዮጵያ መፈታት አለበት በሚሉ በወዳጅ አገሮች ድጋፍ ውድቅ ሆኗል። ይህ የሆነው ለበርካታ ጊዜ ሲሆን፤ አሁንም የሚታየው የጣልቃ መግባት ፍላጎቱ እየጨመረ ነው። ነገር ግን በዚያው ልክ እየተሳካላቸው አይደለም።
አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን ውስጣዊ ችግር በግምባር ቀደምትነት መፍታት ያለበት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ነው። በዚህ ሂደት ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው። ነገር ግን ዓለም አቀፍ ህግጋትን የሚጥስ የውጭ ጣልቃ ገብነት ፍላጎት እየታየ ነው። ጣልቃ ለመግባት የሚሞክሩት የውጭ ኃይሎች በራሳቸው ሀገር እንዲደረግ የማይፈልጉትን ነገር በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ነው ። ይሄም አግባብነት የሌለው ነው።

ምላሽ ይስጡ