የአሸባሪው ቡድን ግልፅ…

የአሸባሪው ቡድን ግልፅ…

  • Post comments:0 Comments
የአሸባሪው ቡድን ግልፅ የሆነ የሽብር እቅድ የያዘው ሰነድ መውጣቱን ተከትሎ የቡድኑን ዋና ዋና እቅዶች በዚሁ ገጽ ላይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ ይህ ቡድን ዛሬም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት የማይቆፍረው ጉድጓድ እንደሌለ በሰነዱ ላይ በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ጥቂት ግለሰቦች ልዩ ጥበቃና ከለላ የሚያስፈልጋቸው የትግራይ ህፃናትን፣ እናቶች፣ አዛውንቶችን መስዋእት አድርገው፤ ወንድማማች ህዝቦችን ደም አቃብተው፤ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተናክሰው፤ ብቻ ከተጠያቂነት ለመዳን በተንኮል በሾለ ጥፍራቸው የማይቧጥጡት ነገር የለም፡፡
ኢትዮጵያ ፈርሳ እነርሱ ቢድኑ፤ ትግራይ ትውልድ አልባ ሆና ዳግም ወደስልጣን ማማ ቢመለሱ መሻታቸው ነው፡፡ ሀገር፣ ታሪክ፣ አንድነት፣ አብሮነት፣ የህዝብ ፍላጎት፣ እውነት የሚባሉ መሰረታዊ መንግስትን ማፅኛ ሀሳቦች ከእነሱ ምቾት በታች ናቸው፡፡ ደንታም አይሰጣቸውም፡፡
በእነርሱ ምክንያት የሚፈናቀለው ህዝብ፣ የሚታረዱት ንፁሃን፣ የሚፈሰው ደም፣ የሚበላሸው ታሪክ፤ በግፍ የሰከረ የጭካኔ ልባቸውን አያራራውም፡፡ በተለይ ባልተረጋጋች ሀገር መፈጠር ውስጥ እናገኘዋለን ብለው የሚያስቡትን የቅዠት ነፃነት ለመጨበጥ ሲሉ የፈፀሙትን ግፍ ወደ ኋላ ዞር ብሎ ላየው እጅግ ያሳዝናል፡፡
በዚህ ብቻ ያላበቃው የእውር ድንብር ጉዟቸውም ዛሬ ላይ ትግራይን ሀገር አደርጋለው፤ ህዝብ አስተባብረን የራሳችንን ሀገር ብንመሰርት ሽምግልናችን በዘይት ይለመልማል ከተጠያቂነት እንድናለን ብለው ያስባሉ፡፡
በዘመናት መሀል ኢትዮጵያውያን ሀገሬ ብለው እንደቅጠል የረገፉባትን የትግራይ ምድር፤ የአያት ቅድመ አያቶቻችን አፅመ እርስት የተጋገረባትን፣ ብዙዎች የተሰዉላት፣ ሀገሬ ተነካች ብለው በትግራይ በኩል ጦር ሲመዘዝ ደረታቸውን የሰጡላትን የኢትዮጵያ መሰረት የሆነችው ትግራይን ጥቂት ማስተዋል የተሳናቸው ማፊያዎች ገንጥለው ሀሳቡን ለመዳኛነት ሊጠቀሙበት ቋምጠዋል፡፡ የህወሓት የሽብር ቡድን ሴራ በኢትዮጵያውያን ትብብር እየተጋለጠ፤ ቅዥት እየሆነ መጥቷል፡፡ ወደፊትም እንሱ እንዳቀዱት ሳይሆን በኢትዮጵያውያን አንድነት የውጩንም ሆነ የውስጥ ጫናዎችን ተቋቁመን የአገራችንን ብልጽግና ማረጋገጣችን አይቀሬ ነው፡፡

Leave a Reply