ወያኔ አቅዶ የከፋፈለውን ህዝብ ሳያስበው አንድ እያደረገ ነው  /በአብዲ ኬ/

ወያኔ አቅዶ የከፋፈለውን ህዝብ ሳያስበው አንድ እያደረገ ነው /በአብዲ ኬ/

  • Post comments:0 Comments

ወያኔ አቅዶ የከፋፈለውን ህዝብ ሳያስበው አንድ እያደረገ ነው

በአብዲ ኬ

የአሸባሪው ህወሃት የክህደት ተግባርና ባንዳነት ይህን ተከትሎም አገሪቱ ያስተናገደችና እያስተናገደች ያለችው ጦርነት በብዙ መልኩ አገርንና ህዝብን እየጉዳ መሆኑ እሙን ነው፡፡

በስሙ ምለው የሚገዘቱት የትግራይ ህዝብ በነሱ እብሪት፤ የስልጣን ጥመኝነትና ስግብግብነት ምክኒያት የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ ሆነ፤ ይህም አልበቃ ብሏቸው ወጣቱን በተሳሳተ ፕሮፖጋንዳቸው ለበቀል አነሳስቶ በጎንደርና በወሎ ህዝብ ላይ የሰው ልጅ በሰው ይቅርና እንስሳ ላይ እንኳን የማይፈጽመውን ሰይጣናዊ ክፋት ፈጽሟል፡፡

በነርሱ ክፋት ሳቢያ በሁለት ጎራ ተሰልፎ ወድ የአገር ልጆች ተሰውተዋል፤ ህዝብ ለስቃይና ለእንግልት ተዳርጓል፡፡

አሁን አሁን ግን ይህ አሸባሪ ቡድን አቅዶ የከፋፈለውን ህዝብ ሳያስበው በሚሰራው ክፉ ስራና በገሃድ በሚያንጸባርቀው የአገር ጠላትነት ተግር በአንድ ጥላ ስር እያሰባሰበ ነው፡፡

ምንም እንኳን አገር ጊዜያዊ ፈተና ውስጥ ብትሆን፤ ከጫፍ እስከ ጫፍ አሁን ያለው የአገራዊ አንድነት ስሜት በችግር ውስጥ ሆነህ እንኳን በአገርህ ተስፋ እንዲኖርህ የሚያደርግ ነው፡፡

ለዚህ ብዙ ማሳያ መጥቀስ ቢቻልም፤ ህዝቡ ለመከላከያ እያሳየ ያለው የደጀንነትና ከለላነት፤ ዋናው የአገር አንድነት ምሰሶ የሆነው ይህ ሰራዊት በስንቅና በትጥቅ የተጠናከረ እንዲሆን ከሌለው ላይ ቀንሶ ሲሰጥ ማየት በራሱ የአገር አፍራሾች ህልም ቅዠት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ወገን ለተፈናቀለው ወገኑ ለመድረስ በየአካባቢው እንቅስቃሴ ሲያደርግ፤ ያገኘውን ይዞ ወደየ ግንባሩና ወደየ ተፈናቃዮች መጠለያ ሲተም ማየት አንዳች የአለኝታነት ስሜት እንዲሰማህ ያደርጋል፡፡

ከዚህም አልፎ በአካል ገብቶ መከላከያን ለማጠናከር በመላው አገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ ወደ ስልጠና ካምፖች የሚተመውን ወጣት ስታይ የአገር ባለቤትነትና ጠባቂነት በተግባር ሲለካ እንዲህ ነው ለካ ያስብላል፡፡

መሰረታዊ የውትድርና ትምህርቶችን በመውሰድ የተመረቁ ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ወኔና የወገን መጠቃት፤ የአገር መደፈር እልህ አስገብቶት ታጥቆ ወደየ ግንባሩ ሲተም ማየት የአሁኑ ትውልድ እንደ አባቶቹ “አገሬ መቼም አትደፈርም” በማለት ገድል ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ያሳያል፡፡

Leave a Reply