You are currently viewing በወሎ ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ

በወሎ ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ

  • Post comments:0 Comments
በወሎ ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ
 
በወሎ ግንባር አሸባሪውን የህወሓት ስብስብ እየተፋለመ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና በጦርነቱ ሳቢያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶችና ሴቶች ሊግ 38 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ።
 
የብልፅግና ፅህፈት ቤት ሲቪክ ማህበራትና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ፓል ቱት የተደረገው ድጋፍ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን ስለመሆናችንና አክብሮታችን ለመግለፅ ያለመ ነው ብለዋል።
 
የብልፅግና ፅህፈት ቤት ወጣቶች ሊግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አክሊሉ ታደሰ በበኩሉ፤ ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ፈተና ሲገጥማት ነበር፤ አሁንም ከውስጥና ከውጭ ፈተና ገጥሟታል። ሆኖም በተለመደው የአሸናፊነት መንፈስ እንወጣዋለን ድጋፋችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።
 
የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም አበበ በበኩላቸው፤ በግንባር ለሚፋለሙ ሰራዊት አባላት ክብራችን የላቀ ነው ድጋፋችንም ይቀጥላል ብለዋል።
 
ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ጀግኖች የምታፈራ መሆኑን ጠቁመው አሁንም በጀግኖቿ ሉዓላዊነቷን አስከብራ እንደምትሄድ እርግጠኞች ነን ነው ያሉት።
 
የወሎ ግንባር ኢንዶክትርኔሽን ዳይሬክተር ተወካይ ሌተናል ኮለኔል ለቺሳ መገርሳ በኩላቸው፤ ህዝብ ይዘን የማናሸንፈው ነገር የለም። በመሆኑም ሊጉ ለተፈናቀሉ ዜጎችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ አንድነት እንደ አሸባሪው ህወሓት ሳይሆን እንደ አብዛኛው ህዝብ ፍላጎት ተጠናክሮ እንደሚሄድ ማሳያ ነው ብለዋል።አሸባሪው ህወሓት በቅርቡ ግብዓተ መሬቱ እንደሚፈፀምም አረጋግጠዋል።

ምላሽ ይስጡ