በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሰባስበው የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሰባስበው የተሰጠ የአቋም መግለጫ

  • Post comments:0 Comments
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሰባስበው የተሰጠ የአቋም መግለጫ
በአገራችን ኢትዮጵያ ተገደን የገባችበትን ጦርነት ከውጭ ጠላትና ከውስጥ ባንዳ የተቃጣብንን የሉዓላዊነት ጦርነት በመመከት ፓርቲዎች መንግስት በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝተው በጥልቅ መክረዋል፡፡መንግስት በልበ ሰፊነት አይቶ ያደረገውን የተናጠል የተኩስ አቁም እየደገፍን አገራችን ላይ የተቃጣውን ጦርነት ሁለንተናዊ ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን እየገለጽን ፓርቲዎቹ የቀረቡትን የውይይት መነሻ ጽሁፎች ገምግሞ አስተያየት ከሰጡ በኋላ ወቅታዊ ሁኔታዊ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡
1. የእናት ጡት ነካሽ የሆኑት ህወኃትና የእንጀራ ልጅ ኦነግ ሸኔ የተባሉ አሸባሪዎች በህዝባችን እና በአገራችን የተከፈቱትን ጦርነት በጽኑ እናወግዛለን፡፡
2. የአገራችን ሉዓላዊነትን ለማስከበር ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከክልል ልዩ ሃይሎች ጋር አብረን በመሆን ለአገራችን እንዘምታለን፤
3. ምዕራባዊያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመዳፈር በእጅ አዙር የሚያደርጉትን ጦርነት በአስቸኳይ አቁሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲቆሙ ጥሪ እናቀርባለን፤
4. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጎረቤት አገር ሱዳንና ግብጽ በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ የሚፈጽሙትን ደባና ሴራ እንዲሁም የሚዳፈሩንን ሉዓላዊነት እንዲያቆሙ እንዲያደርግ ድርጅቱን በአጽንኦት እየጠየቅን የኢጋድ አባል አገሮችን በአገራችን ኢትዮጵያ እየተሰነዘረ ያለውን ወንጀልና ስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲያስቆሙልን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
5. በአገራችን እየታዬ ያለውን የዋጋ ንረትና የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችና ግለሰቦች መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር አድርጎ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፤
6. በችግራችን ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን ለተሰለፋችሁ ወዳጅ አገራት ህዝብና መንግስታት ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እስካሁን ላደረጋችሁልን ድጋፍ ምስጋና እያቀረብን ወደፊትም የተለመደ ትብብራችሁን እና ድጋፋችሁን እንዳይለየን እንጠይቃለን፤
7. ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተቃጣብንን ወረራና ጥቃት የተለመደውን የአበቶቻችንን ጀግንነትና ወኔ የተላበሰው መከላከያ ሰራዊታችንን እና የክልል ልዩ ሃይሎችን አኩሪ ድል እየተቀናጀንና ክብር መስዋዕትነት እየከፈሉ ጠላትን በማሳደድ ይገኛሉ፡፡በመሆኑም ከአብራክ የተከፈሉ ልጆቻችን ለመርደትና ጋሻ ለመሆን ያሳየው አኩሪ ታሪክ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም የአገራችንን ሰላም እስከሚረጋገጥ የጋራ ክንዳችንን በጋራ ለጋራ በማነሳሳት አለኝታ መሆናችንን ምናሳይበት ወቅት በመሆኑ ከጫፍ እስከ ጫፍ ድንበራችን እንድንጠብቅ የአካባቢያችንን ሰላም እንድንቆጣጠር በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
ነሐሴ 29 /2013 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Leave a Reply