You are currently viewing ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲጠፋ ነው- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲጠፋ ነው- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲጠፋ ነው- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲጠፋ መሆኑን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ።
የብልጽግና፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ፓርቲ አመራሮች በጋይንት ግንባር ጨጨሆ ተገኝተው የመከላከያ ሰራዊቱን ተጋድሎ ተመልክተዋል።
አሸባሪው ቡድን በከተሞች ላይ ከፍተኛ በቀል እና እና ውድመት መፈጸሙን የተናገሩት አመራሮቹ÷የቡድኑ አላማም መግደል፣ ማፈናቀል፣ ንብረት መዝረፍ እና ማውደም መሆኑን አንስተዋል፡፡
አመራሮቹ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በአጭር ጊዜ ተባብረን ሙሉ በሙሉ እንደመስሰዋለን ብለዋል።
በቡድኑ የወደሙ የግለሰብ እና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ በቅንጅት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ዛሬ ጨጨሆ የተገኙት የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ከብልጽግና አቶ ዮሀንስ ቧያለው እና አቶ ፈንታ ደጀን፣ ከኢዜማ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ ከአብን አቶ ጣሂር ሙሀመድ እንዲሁም ከአዴሃን አቶ ተስፋሁን አለምነህ ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል ።

Leave a Reply