ሰራዊታችን ዛሬም ነገም ወደፊትም የድልና የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሆኖ ይቀጥላል

ሰራዊታችን ዛሬም ነገም ወደፊትም የድልና የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሆኖ ይቀጥላል

  • Post comments:0 Comments
ሰራዊታችን በየተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ የፈጸማቸውን ገድሎች በሙሉ አንስቶ መጨረስ አይቻልም፡፡ ሰራዊታችን ችግር የማይበግረው፤ ፈተና ከኢትዮጵያዊነቱ ፈቀቅ የማያደርገው ከህዝብ ወጥቶ ለህዝብ የሚኖር ዕንቁ የሀገር ሀብት ነው፡፡
 
ጠላት ሀገርን ሊወር ከሩቅ ሲመጣ ከህዝብ ቀድሞ ግንባሩን ለጥይት የሚሰጥ፣ ለሀገር ኖሮ፣ ለህይወቱ ሳይሳሳ ግንባር ተሰልፎ፣ ለሀገር ተዋግቶ፣ ለሀገር ቆስሎ ለሀገር የሚሞት የኢትዮጵያዊነት መሰረት ነው፡፡ የአገር መከላከያ ሰራዊት፡፡
 
በሰላሙም ጊዜ ህዝብን መስሎ የሚኖር፣ ህዝብ ሲቸገር ቆሞ ማየት የማይችል እንስፍስፍ ልብ ያለው፣ ዜጎች በደም እጦት ምክንያት ህይወታቸው እንዳያልፍ ዳር ድንበሩን እየጠበቀ ደሙን ሳይሰስት የሚሰጥ የህዝባዊነት ምልክት ነው፡፡
ሰራዊታችን በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያልቻሉ ድልድዮችንና መንገዶችን ጉልበቱን፣ ገንዘቡንና ዕውቀቱን አጣምሮ ለህዝብ ጥቅም የሚያውል ከራሱ በላይ ለህዝብ የሚኖር የመልካም ስብዕና ባለቤት ነው፡፡
ጁንታው የህወኃት ቡድን “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” በሚል እሳቤ በሰራዊታችን የሚቃጣበትን ጥቃት መቋቋም ሲሳነው በህዝብ ሀብት የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን ከጥቅም ውጭ ሲያደርግ ተመልክተናል፤አሁንም እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለገብ የሆነው ሰራዊታችን ከዚህ ቀደም በተለያዩ የግዳጅ ግንባሮች እንደሚያደርገው ሁሉ ጠላት የሆነውን አሸባሪውን ህወኃት እየተዋጋ ጎን ለጎን በጥፋት ቡድን ጥቃት የተፈጸመባቸው መሰረተ ልማቶችን እየጠገነ ለአገልግሎት እንዲበቁ ማድረግ የዘወትር ስራው ሆኗል፡፡
 
ሰራዊታችን ከወንድሞቹ ከአማራና ከአፋር ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ጋር በመሆን በዘራፊውና አምባገነኑ የህወኃት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ህዝብ ላይ ምንም አይነት አደጋ እንዳይደርስ እጅግ በረቀቀ መንገድ፣ በተጠናና ብስለት በተሞላበት አካሄድ ብሎም በተመረጠ ሁኔታ አሸባሪውንና ጄሌዎቻቸውን ለይቶ በማጥቃት ኢትዮጵያዊነቱን እና የህዝብ አጋርነቱን በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል፡፡ ሰራዊታችን ዛሬም ነገም ወደፊትም የድልና የኢትዮጵያዊነት ምልክት ሆኖ ይቀጥላል፡፡

Leave a Reply