You are currently viewing አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በትግራይ ያለውን ሁኔታ የዳሰሱበት መንገድ መለያየትን የሚያባብስና ሃላፊነት የጎደለው ነው – ሩሲያ

አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በትግራይ ያለውን ሁኔታ የዳሰሱበት መንገድ መለያየትን የሚያባብስና ሃላፊነት የጎደለው ነው – ሩሲያ

  • Post comments:0 Comments
አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በትግራይ ያለውን ሁኔታ የዳሰሱበት መንገድ መለያየትን የሚያባብስና ሃላፊነት የጎደለው ነው – ሩሲያ
 
በትግራይ ካለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ሁኔታውን የሚያዩበት መንገድ መለያየትን የሚያባብስና ሃላፊነት የጎደለው ሆኖ መታየቱን ሩሲያ አስታወቀች።
 
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሪቫስ እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻና በወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባይዋ በመግለጫቸው አሸባሪው ህወሃት አሁንም ድረስ ወደ ውጊያ በመግባት ወደ አፋር እና አማራ አጎራባች ክልሎች ጥቃት በመሰንዘር የሰብአዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል ማድረጉንና የኢትዮ-ጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ጥቃት መፈጸሙን ገልጸዋል።
 
“ቡድኑ ከክልሉ በማለፍ ያደረሰው ጭፍጨፋና ጥቃት ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈለጋቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ድጋፍ እንዳያገኙ አድርጓል” ብለዋል።
“ለእነዚህ ችግሮች መከሰት የአንዳንድ የምዕራባውያን የሚዲያ አካላት ሚናም ከፍተኛ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል” በማለት ያብራሩ ሲሆን፤ የእነዚህ አካላት እንቅስቃሴ ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሀላፊነት በጎደለው ተግባር ጥፋትን ማባባስና ልዩነቶችን የማቀጣጠል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
“ደም መፋሰሱን ለማስቆም፣ የሰብአዊ ሁኔታን ለማሻሻል፣ ማህበረ-ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠርና ተፈናቃዮችን ወደ ቋሚ መኖሪያቸው ለመመለስ በሁለቱም በኩል የተኩስ አቁም ማወጅ ብቸኛው አስተዋይ መንገድ ነው ብለን እናምናለን” ነው ያሉት።
“በትግራይ ክልል ሰላምን ለማምጣትና ወደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ለመመለስ በኢትዮጵያ መንግስት እየተከናወነ ያለውን ተግባር አለም አቀፉ ማህበረሰብንና ቀጠናቂ ተቋማትን እንዲደግፉ ጠሪ እናቀርባለን ሲሉም አስታውቀዋል።
“ሩሲያ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳያቸውን ከአፍሪካውያን ጋር በራሳቸው ለመፍታት ወሳኝ ሚና መጫወት አለባቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ምላሽ ይስጡ