You are currently viewing ብልፅግና ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የ14 አቅመ ደካማ እናቶችን ቤት ሊገነባ ነው

ብልፅግና ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የ14 አቅመ ደካማ እናቶችን ቤት ሊገነባ ነው

  • Post comments:0 Comments
ብልፅግና ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የ14 አቅመ ደካማ እናቶችን ቤት ሊገነባ ነው
የክረምት በጎ ፍቃድ አካል የሆነው የአቅማ ደካሞችን ቤት የማደስ ሰራ በክረምቱ መግቢያ ላይ በፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብይ አህመድ አስጀማሪነት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።
ባለፉት የክረምት ወራትም የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም በባለሃብቶች በሺዎች የሚቆጠሩ አቅመ ደካሞች ቤት ማደሳቸው ይታወቃል።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ 14 አቅመ ደካማ እናቶችን ቤት የማደስ ስራ ዛሬ አስጀምሯል።
ቤቶቹ ከፍ ባለ ጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ሲባል እንዲሁም ዜጎች በምቹ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ የፓርቲው ዋና አላማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ለቤት ግንባታ ፕሮጀክቱ በጀት ተመድቧል።

ምላሽ ይስጡ