የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ነው፦ ኮሎኔል የሺበር አዳነ

የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ነው፦ ኮሎኔል የሺበር አዳነ

  • Post comments:0 Comments
የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ነው፦ ኮሎኔል የሺበር አዳነ
የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል በማይጠብሪ ግንባር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ ተናገሩ።
በማይጠብሪ ግንባር ለዳግም ወረራ የተነሳው አሸባሪውና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ እየተደመሰሰ መሆኑን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጋዜጠኞች ቡድን በግንባር ተገኝቶ ተመልክቷል።
በማይጠብሪ ግንባር ያነጋገርናቸው የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር አዳነ እንደገለጹት ሽብርተኛው ትህነግ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጠላትን ለማሸነፍ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ መግባቱ እየተመዘገበ ላለው ድል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ኮሎኔል የሺበር አስታውቀዋል።
ኮሎኔሉ ሽብርተኛው ትህነግ ከዓመታት በፊት የቀየሰውን የጦርነት ስልት እየተከተለ መሆኑን ነው የተናገሩት። ዋና አዛዡ አሸባሪው ቡድን በአሁኑ ወቅት ጦርነቱን በመሣሪያ ሳይሆን በሰው ማዕበል ለመምራት ጥረት እያደረገ ነው፤ አቅሙም እየተዳከመ መጥቷል፤ የትግራይ ወላጆችም ልጆቻቸው የእሳት ራት ከመሆናቸው በፊት ሊታደጓቸው ይገባልም ብለዋል።
እንደ ኮሎኔሉ ገለጻ በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጠንካራ ክንድ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት እየተደመሰሱ ነው፤ ሠራዊቱ በቀጣይም ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅ በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል፤ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ኃይሉ ጠንካራ አደረጃጀት ድል እንዲያስመዘገብ አስችሎታል ብለዋል፡፡ ጠላትም በገባበት እንዲቀር እንዳደረገው እና የህልውና ዘመቻው በቅርቡ በአመርቂ ውጤት ይደመደማል ነው ያሉት ኮሎኔሉ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል ጠላትን ለመደምሰስ በሚያደረገው ተጋድሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቋረጠ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል።
ሠራዊቱ ሰንሰለታማ ተራሮችን ተጋፍቶ እያሸነፈ የመገስገሱ ምስጢርም ሕዝባዊ ደጀን በመኖሩ ነው ብለዋል። ሕዝቡም በቅርቡ ወደ ተረጋጋ ሰላም እንደሚመልስም የ54ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሺበር ገልፀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

Leave a Reply