በተደራጀና በተናበበ ህዝባዊ ንቅናቄ አሁን ያጋጠመንን ችግር እንመክታለን፤ቀልብሰን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እናወጣለን-ተስፋዬ ቤልጂጌ

በተደራጀና በተናበበ ህዝባዊ ንቅናቄ አሁን ያጋጠመንን ችግር እንመክታለን፤ቀልብሰን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እናወጣለን-ተስፋዬ ቤልጂጌ

  • Post comments:0 Comments

በተደራጀና በተናበበ ህዝባዊ ንቅናቄ አሁን ያጋጠመንን ችግር እንመክታለን፤ቀልብሰን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እናወጣለን-ተስፋዬ ቤልጂጌ

ለውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በሚንስትር ማዕረግ የምርጫና የዲሞክራሲ ግንባታ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዛዲግ አብርሃ በሰሜን በኩል የተከፈተው ጦርነት ከኢትዮጵያዊያን ፍላጎት ውጭ የስርዓት ለውጥ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቅሰው የኢኮኖሚ አሻጥር እንዲፈጠር በማድረግ ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ ተማሮ መንግስት ላይ ለማነሳሳት እየሰሩ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ዛዲግ አያይዘውም እንደ አገር የመጣውን ሁለንተናዊ ለውጥ ለመቀልበስና ያለፈውን ጨቋኝ ስርዓት ለመመለስ አሸባሪው የህወኃት ቡድን የሞት ሽረት እያደረገ በመሆኑ ጊዜ ሳናባክን ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ቋጭተን ወደ መደበኛ የልማት ስራዎቻችን ልንመለስ ይገባል ብለዋል፡፡

ከጂኦ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ ሁለተኛውን የውይይት መነሻ ሃሳብ እና መድረኩን የመሩት በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በበኩላቸው በተደራጀና በተናበበ ህዝባዊ ንቅናቄ አሁን ያጋጠመንን ችግር እንመክታለን፤ቀልብሰን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እናወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ አያይዘውም አሸባሪው የህወኃት ቡድን ዓላማ ኢትዮጵያ ውስጥ ደካማ መንግስት እንዲፈጠር በማድረግ የምዕራባዊያን ተላላኪ ማድረግና ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢንድሪስ የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያዊያን እርዱን አግዙን አለበለዚያ ግን የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን እንድንፈታ በውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ ጣልቃ እንድትገቡ አንፈቅድም ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመወከል በውይይቱ የተገኙት ፕሮፌሰር እያሱ በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ የደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ቤተ ክርስቲያኗን በእጅጉ ያሳዘነ መሆኑን ጠቅሰው መንግስት ህግ ለማስከበር እያደረገ ያለውን ዘመቻ እንደግፋለን ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወክለው የተገኙት መላከ ህይወት አባ ገብረ ጊዮርጊስ ሲሆኑ በሐይማኖት ጥላ ስር ተጠልለው ለአሸባሪው የህወኃት ቡድን የሚሰሩ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰው መንግስት ፍተሻ ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልጅ መስፍን ሽፈራው የተገኙ ሲሆን አሸባሪው የህወኃት ቡድን በህዝብ የተመረጠውን ስርዓት በማፍረስ የተለመደውን አፋኝ ስርዓት ለመመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ይህ ደግሞ መቼም አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ለመሳተፍ ከሲዳማ ክልል የተገኘችው ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ አሸባሪው የህወኃት ቡድን የጦር መሳሪያዎችን በዕምነት ተቋማት በመከዘን የእምነት ቦታዎችን ላልተፈለገ ዓላማ ያዋለ ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ፋንታዬ አያይዘውም ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን ተግዳሮት አልፋ የተረጋጋች አገር እንድትሆን እያንዳንዳችን ከመንግስታችን ጎን በመሰለፍ ድምጻችንን ልናሰማ ይገባልም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም አሸባሪውን የህወኃት ቡድን ለመደምሰስ እየተደረገ ያለውን ትግል ከሰራዊታችን ጎን ሆነን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ በደም ልገሳ፣ድምጹን በሰላማዊ ሰልፍ በመግለጽ፣ዕድሜው የደረሰ ወጣት በሙሉ ሰራዊቱን እንዲቀላቀል መስራትና በተለያዩ ነገሮች ማገዝና በተደራጀ መንገድ ማስተባበር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል መንግስት ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ከአንድ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ከተለያዬ ተቋማት የተወጣጡ የሐይማኖት አባቶች፣ምሁራን፣አርቲስቶች፣ከንግዱ ማህበረሰብ፣ከመምህራን ማህበር፣ከሰራተኞች ማህበር፣ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ከመላው የአገሪቱ ከፍሎች ከተወጣጡ ወጣቶች እና ሴቶች መገኘታቸው የተገለጸ ሲሀን ይህን አይነት መሰል የውይይት መድኮች በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

 

 

Leave a Reply