You are currently viewing ዶ/ር አለሙ ስሜ እና ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ በግንባር በመገኘት የሃገር የቁርጥ ቀን ልጆችን አበረታቱ

ዶ/ር አለሙ ስሜ እና ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ በግንባር በመገኘት የሃገር የቁርጥ ቀን ልጆችን አበረታቱ

  • Post comments:0 Comments
ዶ/ር አለሙ ስሜ እና ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ በግንባር በመገኘት የሃገር የቁርጥ ቀን ልጆችን አበረታቱ
 
በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ዓለሙ ስሜ እና የአብን ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ በወሎ ግንባር በመገኘት ከጠላት ጋር በመዋደቅ ላይ የሚገኙ የሀገር የቁርጥ ቀን ልጆችን አበረታቱ።
ሁለቱ የፖለቲካ መሪዎች አሸባሪው ቡድን በሀገር ላይ የከፈተውን ጥቃት ያለልዩነት መመከት ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች ህብረት በመፍጠር ሀገር ለማፍረስ እየሰሩ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ዓለሙ÷ ይህም ፍፁም የማይሰምር እና በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ የሚመከት ነው ብለዋል።
በግንባሩ በርካታ የጁንታው ተላላኪዎችና ሰርጎ ገቦች እየተደመሰሱ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን÷ ይህም ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ እያገኘ መሆኑን አስረድተዋል።
ጦርነቱ በአጭር ጊዜ በድል ተጠናቆ ሀገር ወደቀደመ ሰላምና ልማቷ እንድትመለስ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ፖለቲከኞቹ÷ ያለልዩነት በመሰራት ላይ ያሉ ስራዎችም ልብን የሚያሞቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ሁለቱ አሸባሪዎች ሸኔና ወያኔ የፈጠሩት ያልተቀደሰ ጋብቻ ከዚህ ቀደምም የነበረ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይህም ከዚህ በፊት ውጤት ያላመጣ ወደፊትም የማያመጣ ነው ብለውታል።
የአብን ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ካሳ በበኩላቸው÷ ምንም እንኳን የፖለቲካ ምልከታ ልዩነቶች ቢኖሩም ኢትዮጵያዊያን የተቃጣባቸውን የህልውና አደጋ ለመመከት እየሰሩ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ አያሌ ፈተናዎችን ማለፏን የተናገሩት ረዳት ፕሮፌሰሩ÷ ያለልዩነት የተሰሩ ስራዎች በድል ላይ ድል እየደረቡ ሄደዋል ነው ያሉት።

ምላሽ ይስጡ