You are currently viewing የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይልን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይልን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments
የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይልን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ
 
የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ተካሄደ።
በሰልፉ ላይ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ የሶማሊ ብልፅግና ፅ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ሌሎች አመራሮች እና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
 
በጅግጅጋ ከተማ እስታዲዬም በተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍና አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ የሚያወግዙ የተለያዩ መልክቶችን አስተላልፈዋል።
 
በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ ከሚገኙ 20 ቀበሌዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ በመውጣት አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ቡድን ሀገር የማፍረስ ተግባር የሚቃወምና የሀገር መከለከያ ሠራዊትና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይልን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
 
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን አንግበው ለመከላከያ ሠራዊትና ለሶማሊ ልዩ ሀይል ያላቸውን ድጋፍ የገለፁ ሲሆን የሀገርና ህዝብ ጠላት የሆነውን አሸባሪውን የህወሐት ቡድን በሀገሪቱ ላይ የከፈተውን ጦርነት አጥብቀው እንደሚቃወሙ ገልፀዋል።
 
አሸባሪው ህወሐት የሀገሪቱ ንፁሀን ዜጎችን በመግደልና በመጨፍጨፍ ታሪክ ይቅር የማይለው የጥፋት ተግባር እፈፀመ መሆኑን የሚገልፁት በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ይህ የሀገር ነቀርሳ የሆነው የጥፋት ቡድን በተባበረ ክንድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊነቀል ይገባል ብለዋል።
 
አሸባሪው የህወሓት ቡድን ባለፉት 30 አመታት በሶማሊ ክልል ህዝብ ላይ የፈፀመው አስከፊ በድሎች ከህሊናችው መቼም እንደማይጠፋ የተናገሩት ነዋሪዎች አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሌሎች የሀገሪቱ የፀጥታ አካላትና ከህዝቡ ጋር ተሰልፈው የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ ለማድረግና የህይወት መሰዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
 
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለረጅም ጊዜ ሲሰራ የቆየውን ኢትዮጵያዊያን የማፍረስ እቅድ ለማሳካትና ዳግም የማእከላዊ መንግስት ስልጣን ላይ ለመውጣት የተለያዩ የጥፋት ተግባር እየፈፀመ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ዜጋ በአንድነት ሆነው የጥፋት ቡድኑን ለማጥፋት ሊረባረቡ ይገባል ብለዋል።
 
ጁንታው ሀገር የማፈረስ አቅም የለውም ያሉት የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ይህንን የጥፋት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብአተ መሬቱን በመፈፀም የሀገሪቱን ሰለም ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።
 
የሶማሌ ህዝብ ባለፉት 30 አመታት በጁንታው የተጎዳ ህዝብ መሆኑን የጠቆሙት ርእሰ መስተዳደሩ የክልሉ ህዝብ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማጥፋት ከመላው የሀገሪቱ ህዝብ ጎን ተሰልፎ የሚጠበቅበትን ተጋድሎ ያደርጋል ብለዋል።
 
ወቅቱ የመላው የሀገሪቱ ህዝቦች አንድነት የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ ህብረተሰቡ በየአከባቢው ግጭትና መከፋፈል የሚፈጥሩ ሀይሎችን እኩይ ሴራ በማክሸፍ በፍቅርና በአንድነት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ርእሰ መስተዳድሩ ጠቁመው የክልሉ መንግስት አሻበሪው ህወሃትን ለመደመሰስ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩሉን ድጋፋ ያበረክታል ብለዋል።

ምላሽ ይስጡ