አሸባሪው የህወኃት ቡድን ህዝቡን ለአገዛዝ እንዲመቸው በዘር፣ በጎሳና በሀይማኖት እየከፋፈለ እና አጀንዳ እየፈጠረ እርስ በእርስ ሲያጋጭ የኖረ ቡድን ነው- ወ/ሮ መስከረም አበበ

አሸባሪው የህወኃት ቡድን ህዝቡን ለአገዛዝ እንዲመቸው በዘር፣ በጎሳና በሀይማኖት እየከፋፈለ እና አጀንዳ እየፈጠረ እርስ በእርስ ሲያጋጭ የኖረ ቡድን ነው- ወ/ሮ መስከረም አበበ

  • Post comments:0 Comments
አሸባሪው የህወኃት ቡድን ህዝቡን ለአገዛዝ እንዲመቸው በዘር፣ በጎሳና በሀይማኖት እየከፋፈለ እና አጀንዳ እየፈጠረ እርስ በእርስ ሲያጋጭ የኖረ ቡድን ነው- ወ/ሮ መስከረም አበበ
 
ነሀሴ 07/2013 (ብልጽግና )ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት በብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም አበበ ህዝቡን ለአገዛዝ እንዲመቸው በዘር፣ በጎሳና በሀይማኖት እየከፋፈለ እና አጀንዳ እየፈጠረ እርስ በእርስ ሲያጋጭ በኖረው በአሸባሪው የህወኃት ቡድን ምክንያት በርካቶች ተፈናቀለዋል፤ለስደት እና ለእንግልት ከመዳረጋቸውም በላይ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
ኃላፊዋ አያይዘውም በሀገራችን የተፈጠረውን የለውጥ ጉዞ ባለመቀበል እና ኢትዮጵያን እኔ ካልመራኋት ትፍረስ የሚል አቋም በመያዝ የህዝቡን ሰላማዊ ኑሮ ለማደፍረስ በተለያዩ የአገሪቱ ቦታዎች ትንኮሳውን ከመፈጸሙም ባሻገር ሀገራችን የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማደናቀፍ ዛሬም ድረስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
 
አሸባሪውን የህወኃት ቡድን ለመደምሰስ ግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ፣በአይነትና በገንዘብ ሃብት ማሰባሰብ መቻሉን ያወሱት ወ/ሮ መስከረም የሊጋችን አባላት እና መላው የሀገራችን ሴቶች የተደቀነብንን የሀገር የማፈረስ ዘመቻና የውክልና ጦርነት ለመመከት አቅማችንን መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
በመጨረሻም የትግራይ እናቶች ለጥቂት ሰዎች ፍላጎት ብላችሁ እራሳችሁን ሆነ ልጆቻችሁን ከአሸባሪው የህወኃት ቡድን ሴራና ተንኮል በማራቅ ልጆቻችሁን ካላስፈላጊ መስዋዕትነት እንድትጠብቁ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ አሸባሪውን የህወኃት ቡድን በመቅበር ኢትዮጵያን ወደ ሰላሟ፣ አንድነቷ እና ልማቷ እንድትመለስ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

Leave a Reply