You are currently viewing ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣው አሸባሪው ሀይል በመደምሰስ ላይ ይገኛል- የመከላከያ ሰራዊት

ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣው አሸባሪው ሀይል በመደምሰስ ላይ ይገኛል- የመከላከያ ሰራዊት

  • Post comments:0 Comments
ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣው አሸባሪው ሀይል በመደምሰስ ላይ ይገኛል- የመከላከያ ሰራዊት
ደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለጦር ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣው አሸባሪው የጁንታ ሀይል በጉባላፍቶ ወረዳና አካባቢው በመደምሰስ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ እንደገለፁት÷ አሸባሪው ሃይልና ርዝራዦቹ ትላንት የመከላከያ ሠራዊት የደረሠበትን ቅጣት በመዘንጋት ዳግም የቅዠት ህልሙን አሣካለሁ ብሎ ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ እንቅሥቃሤ ለማድረግ ቢሞክርም በ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ሣንቃ በተባለውና በጉባላፍቶ ወረዳአካባቢ የሽብር ቡድን አባላትን መደምሰስ ተችሏል።
ጁንታው ወልድያን ተቆጣጥሪያለሁ ያለውን ሀሰተኛ ወሬ በማሥታወስ በአሁኑ ሠዓት ወልድያ ላይ ሁነን እንኳን የሀሰት ወሬውን በመንዛት ይህንን አካባቢ ተቆጣጥሪያለሁ እያለ ህዝብን የሚያሸብር ተግባሩን እንደ የአንድ የጦርነት ሥልት እየተጠቀመበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም ህዝቡ በአሸባሪው “የበሬ ወለደ”ወሬ ሣይደናገርና ሣይረበሽ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ህዝባዊ ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ።
የ21ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት አሁንም በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ ሆኖ ተልዕኮውን በድል ለመወጣት የመንግሥትን ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ አዛዡ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምላሽ ይስጡ