You are currently viewing የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ምንም በማያውቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ባደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል

የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ምንም በማያውቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ባደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል

  • Post comments:0 Comments
የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ምንም በማያውቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ባደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸባሪው የህውሃት ቡድን በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ በጋሊማኮ ጊዜያዊ መጠለያ በነበሩ ምንም በማያውቁ ንፁሃን ዜጎች ላይ ለደረሰው ሞት ፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።
መላው የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎቻችን አንድ ሆነው ይህን ፀረ ህዝብ አሸባሪ ቡድን እስከ መጨረሻው ለማጥፋትና የጀመርነው ትግል አጠናክረን እንደምንቀጥል ቃላችንን በድጋሚ እናድሳለን።
ስለሆነም የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አሸባሪው የህውሓት ቡድን የህዝቦችን ወንድማማችነት ለመሸርሸርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የያዘው ከንቱ ምኞት እንዳይሳካ የህዝባችንን አንድነት በማጠናከርና ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ደጀን በመሆን በንቃትና በትጋት መስራቱን እንደሚቀጥልና ኢትዮጵያን ለማዳን የሚደረገው ትግል የሚጠይቀውን ማንኛውም መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ
ነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀረር

ምላሽ ይስጡ