You are currently viewing ቻይና የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

ቻይና የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

  • Post comments:0 Comments
ቻይና የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች
 
ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሀገሮች የምታደርገውን የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች።
የኮቪድ 19 ክትባት ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክ የመጀመሪያው ስብሰባ በቪዲዮ ኮንፈረስ የተካሄደ ሲሆን፥ በዚህ መድረክ ላይ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ንግግር አድርገዋል።
በመድረኩም ፕሬዝዳንት ዢ ኮቪድ -19 ወረርሽኝ አሁንም እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም ቻይና ዓለም አቀፍ የጤና ማህበረሰብን ለመገንባት ክትባቶችን ለዓለም ሀገራት በተለይም ለታዳጊ አገሮች ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም ሀገራቸው በክትባት ምርት ላይ ያላትን ትብብር በንቃት እያሳደገች ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በመሆኑም ቻይና ታዳጊ አገሮች ቫይረሱን እንዲቋቋሙ ለመርዳት የቻለችውን ሁሉ በማድረግ ትቀጥላለች ብለዋል።
ቻይና በዚህ ዓመት በመላው ዓለም ሁለት ቢሊየን የኮቪድ 19 የክትባት መጠን በዓለም አቀፍ ተደራሽ ለማድረግ ትሰራለችም ነው ያሉት።
በተጨማሪም ለ ኮቪድ 19 የክትባት (COVAX) ተቋም 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመስጠት ትጥራለች ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም ዓለም አቀፋዊ የህዝብ ጥቅም እና እንዲሁም በ ኮቪድ ላይ ለዓለም አቀፍ ትብብር አዲስ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
ቻይና ክትባቶችን ለዓለም አቀፉ ህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነትን ለማክበር እና በኮቪድ 19 ላይ ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ትብብር አዲስ አስተዋፅኦ ለማድረግ ሌላ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በበኩላቸው ፥ ኢ-ፍትሃዊ ስርጭት እና ያልተመጣጠነ ክትባት ዋና ተግዳሮቶች ሆነው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።
ይህ ተግዳሮትም ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ነው ያሉት።
ለዚህም አንድ ሆነን ተባብረን ከመሥራት ሌላ አማራጭ የለንም።
ዋንግ ቻይና እስካሁን ከ100 ለሚበልጡ አገራት ክትባት መለገሷን ጠቁመው ፥ ከ 770 ሚሊየን በላይ የመድኃኒት ክትባቶችን ከ 60 በላይ አገራት መላኳንም ተናግረዋል ።
ቻይና እና ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 እርስ በእርስ ሲደጋገፉ መቆየታቸውን ገልጸው፥ይህምበ ወረርሽኙ ላይ የቻይና አፍሪካን አብሮነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
ቻይና በተለያዩ መንገዶች ኢትዮጵያ ቫይረሱን እንድትቋቋም መርዳቷን ትቀጥላለች በዚህም ቻይና የለገሰችው እና ልትለግሰው የምትፈልገው የክትባት መጠን 1 ሚሊየን ደርሷል ብለዋል።
ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገው የሚቀጥለው የክትባት ድጋፉም በነሐሴ ወር አዲስ አበባ እንደሚደርስ መናገራቸውን አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምላሽ ይስጡ