አገር በማዳን ተልእኮ መላው አባላችን እንዲሁም አገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ በትዊተር እና ሌሎች የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖበታል
በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ለሁለት ቀናት ያህል የ2013ዓ/ም አፈፃፀምና የ2014 ዓ/ም ዕቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።
ውይይቱም ሃገራችን የተደቀነባትን ወቅታዊ አገራዊ አደጋ በህዝብ ግንኙነት ዘርፍ በምን መልኩ ማገዝ ይኖርብናል በሚል አጀንዳ ዙርያም ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ክ/ከተሞች ሪፖርታቸውን በማቅረብ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶችም ለቀጣይ ትምህርት በሚወሰድበት መልኩ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ተይባ ሎና እየተገባደደ የሚገኘው 2013 ዓ/ም መዋቅር ከመዘርጋት ጀምሮ ለውጡን የሚመጥን የህዝብ ግንኙነት ስራ ለመስራት እርብርብ የተደረገበት ዓመት መሆኑን ገልፀዋል።
ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ዓላማ በሀላፊነት የሚጠበቁ ዜጎች ለአገር ሰላምና ለአገር ግንባታ በጎ ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑን ያስረዱት ሀላፊዋ ሁሉም በእጅ ስልኩ በቀላሉ መጠቀም እየቻለ አቅሙን ማባከንና መድረኩን የጥፋት ሀይሎች በብቸኝነት እንዲፈነጩበት መተው ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
የነበሩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት በሙሉ አቅም ለመንቀሳቀስ የ2014ዓ/ም ዕቅድንም የሚያዳብር ውይይት መደረጉን አመላክተዋል።
በቀጣም መላውን መዋቅር በንቃት ማሳተፍ ፤የብልፅግና ጉዟችን መሰረት የሚጣልበት አመት በመሆኑ የዘርፉ ሚና ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
ህብረተሰቡን በቂ መረጃ ማድረስ የጥፋት ሃይሎን በብቃት መመከትና ለአለም ማህበረሰብ በትዊተር እውነታውን ለማሳወቅ መረባበረብ ይኖብናል፡፡
ለከተማችንና ለአገራችን ሰላምና ብልፅግና የድርሻቸውን ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ እንደሚረባረቡ በየደረጃው የሚገኙ የውይይቱ ተሳታፊ የዘርፉ አመራሮች አረጋግጠዋል።